ኩባንያችን 8ኛውን ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በይፋ አስጀመረ!
ኩባንያችን የአረንጓዴ ኦፕሬተርነት ጉዞውን በማጠናከር፣ ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ “ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል 250 ሺህ ችግኞችን በስኬት ተክሏል፡፡ በዚህም በአዲስ አበባ እንጦጦ (ቁስቋም ማዞሪያ) እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች አረንጓዴ አሻራችንን አሳርፈናል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፤ ይህ ተግባር ኩባንያችን በዘላቂነት ስትራቴጂው (Sustainability Strategy) የሚያከናውናቸው ተግባራት አካል ሲሆን፣ ባለፉት ሰባት ዓመታት ከተተከሉ ከ4.6 ሚሊዮን በላይ ችግኞች 82.7% እንዲጸድቁ መደረጉን አብራርተዋል።
በተጨማሪም በታዳሽ የኃይል ኢንቨስትመንቶች፣ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ የኔትወርክ መሠረተ-ልማቶች እና ኃይል ቆጣቢ አረንጓዴ የዳታ ማዕከላት አማካኝነት የካርቦን ልቀት ቅነሳን ማሳካት ተችሏል። በተመሳሳይ በገነባናቸው ከ9 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያዎች ከ481 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን በማስተናገድ፣ ከ15.4 ሚሊዮን ኪሎግራም በላይ የካርቦን ልቀትን መከላከል ተችሏል፤ ይህም ከ76 ሺህ በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር እኩል ፋይዳ አለው።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በመርሃ-ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮ ቴሌኮም ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ለመንከባከብ ትኩረት የሚሰጥ ተቋም መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞች ወደ ጫካነት መቀየራቸውን በመጥቀስ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በ8ኛው ዙር መርሃ-ግብር ለተከላና እንክብካቤ ሥራዎች ከ2,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጠር ሲሆን፣ ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ ከ24.8 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በንቃት ለተሳተፋችሁ የኩባንያችን ቤተሰቦች፣ አጋሮቻችን እና የመትከያ ቦታ ላመቻቻችሁ የመንግስት አካላት ምስጋና እናቀርባለን፡፡
ለበለጠ፡ https://bit.ly/4xhlXxF
#digitalethiopia #digitalafrica #gsma #itu #worldbank #oecd #g6countries

1 day ago