(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር የሁለቱን አገራት አንድነት የሚያስተዋውቅ ፕሮግራም መካሄዱን የትግራይ ክልል ሚዲያዎች ዘገቡ፡፡ በህወሀት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ትግራይ ክልል አስተዳደር ሚዲያዎች ዛሬ ባቀረቡት ዘገባ ‹‹የሁለቱን ህዝቦች አንድነት የሚያስተዋውቅ ፕሮግራም ተካሂዷል›› ብለዋል፡፡
እንደዘገባዎቹ ፕሮግራሙ የተካሄደው በኢትዮጵያ ወሰን ትግራይ ክልል ውስጥ ነው፡፡ በፕሮግራሙ ከኤርትራ የጉሉምህዳ፣ ዛላንበሳና ሰንአፌ ወረዳዎች ሀላፊዎችና ተወካዮች መገኘታቸውንም አስረድተዋል፡፡ የጉሎምህዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀፍቶም ባራኪ ባደረጉት ንግግር ‹‹የኤርትራና የትግራይ ህዝብ ታሪክ፣ በአመጣጥ፣ በባህልና በማንነት ተመሳሳይ የሆነ አንድ ህዝብ ነው›› በማለት መናገራቸውን የጠቀሱት ዘገባዎቹ ሁለቱ ህዝቦች በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል፡፡
የሰናፌ ዞን አስተዳዳሪው ኢድሪስ አሊ በበኩላቸው ሁለቱ ህዝቦች በጋራ ከመስራትና ከመልማት ተቆጥበው መቆየታቸውን ጠቅሰው ያጡትን ይህንን እድል መመለስ እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን አስረድተዋል፡፡ የትግራይ ምስራቃዊ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ፍስሀ ሀይሌ ሲናገሩ ደግሞ ‹‹የኤርትራና የትግራይ ህዝቦች በጋራ ጠላትን ፊት ለፊት መጋፈጥንና በሰላም አብሮ መኖርን ባህል አዳብረዋል፡፡›› ካሉ በኋላ በህይወት ጉዞ ውስጥ ምንም ችግር ማጋጠሙ የተለመደ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ጨምረውም ሁለቱም ህዝቦች ችግሮቻቸውን በማረምና ስህተቶች እንዳይደገሙ በመስራት የተሻለ ሰላምና ልማት ማረጋገጥ እንደሚችሉ መግለፃቸውን ሚዲያዎቹ ዘግበዋል፡፡

6 days ago