''መጽሐፍ ቅዱስ በተገኘበት ይነበብ” — ፕሬዚዳንት ናይብ ቡኬሌ
#ethiopia | የኤል ሳልቫዶር ፕሬዚዳንት ናይብ ቡኬሌ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ሙሉ ነፃነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ያላቸውን ጽኑ ድጋፍ ገለጹ።
ተማሪዎች በትምህርት ቤት ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያነቡ ይፈቀድላቸው እንደሆነ በአንድ ህፃን የቀረበላቸውን ጥያቄ መሠረት በማድረግ ምላሽ የሰጡት ፕሬዚዳንቱ፣ እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በነፃነት የማንበብና የመረዳት መብት እንዳለው ገልጸዋል።
አክለውም የመጽሐፍ ቅዱስ ተዳራሽነት በትምህርት ቤቶች ብቻ መወሰን እንደሌለበት የጠቆሙት ቡኬሌ፣ ማረሚያ ቤቶች በርካታ ሰዎች ተስፋን፣ ይቅርታንና የሕይወት ለውጥን የሚሹበት ስፍራ በመሆናቸው በዚያም ቢሆን የእምነት መሪዎችና መጋቢዎች የእግዚአብሔርን ቃል የማድረስ አገልግሎታቸው ሊጠበቅለት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

8 days ago