በግብፅ ወደብ ላይ የአሜሪካ ንብረት በሆነ የጋዝ ጫኝ መርከብ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ‼️
በግብፅ የሜዲተራኒያን ወደብ በሆነው ዳሚየታ በሚገኝ የአሜሪካ ንብረት በሆነ ፈሳሽ ጋዝ የሚቀይርና የሚያከማች መርከብ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የእሳት መከሰቱንና በኋላም እሳቱ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሌላ መርከብ መሸጋገሩን ሮይተርስ ዘግቧል።
የብሪታኒያው የባህር ላይ ደህንነት ተቋም አምብሬይ የመጀመሪያ ደረጃ ምዘና እና የደህንነትና የንግድ መረጃዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ 'ኤነርጎስ ዊንተር' (Energos Winter) የተባለችው መርከብ የቀኝ ጎኗ በድሮን ጥቃቱ ተመቷል።
በመቀጠልም እሳቱ በወደቡ ላይ ወደነበረችው 'ጋስሎግ ሳሌም' (Gaslog Salem) ወደተባለች ሌላ የጋዝ መርከብ ተዛምቷል።
በግምት 138,250 ኩቢክ ሜትር የማከማቸት አቅም ያላት 'ኤነርጎስ ዊንተር'፣ መቀመጫው አሜሪካ ለሆነው 'ኤነርጎስ ኢንፍራስትራክቸር' የተባለ ኩባንያ ንብረት ስትሆን፤ የቴክኒክ፣ የደህንነት እና የንግድ እንቅስቃሴዎቿ የሚመሩት ደግሞ በ'ቪልሄልምሰን ሺፕ ማኔጅመንት' ነው።
Seledadotio

9 days ago