ያከተመው የዓባይ ብቸኛ ባለቤትነት ትርክት
*******************
ሰሞኑን እያየነው ያለነው የግብፅ ውኃ-ተኮር ሩጫ ሀገሪቱ ለዘመናት ራሷን ስታሞኝበት የኖረችው የውሸት ትርክት ወደ ፍጻሜው መቃረቡን የሚያሳይ ነው።
ካይሮ ሤራዋ በዲፕሎማሲው መድረክ ውኃ አላነሳ ሲላት፣ የቀጣናውን ሀገራት መሠረት ያደረጉ አዳዲስ ወታደራዊ እና የጸጥታ ትብብሮችን ለመፍጠር በመፍጨርጨር ጊዜዋን እያባከነች ነው።
የሰሞኑ ሩጫዋ ያረጀ እና ያፈጀ የውኃ የበላይነቷን በማወናበድ ለማስቀጠል የምታደርገው የመጨረሻ ሙከራዋ ይመስላል።
ሆኖም ይህ እርምጃዋ አንድን መሠረታዊ እውነት ዘንግቷል፤ እርሱም ኢትዮጵያ በገዛ ሀብቷ ላይ ያላትን ተፈጥሯዊ እና ሉዓላዊ መብት ወደኋላ መመለስ የማይቻል መሆኑን ነው።
የዓባይ ወንዝ በዓለም ታሪክ ውስጥ የሥልጣኔ መገኛ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ይሁን እንጂ የዚህ ታላቅ ወንዝ የ85 በመቶ ውኃ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በተዛባ ትርክት በገዛ ወንዟ ላይ ባይተዋር እንድትሆን ተደርጋ ኖራለች። ይህም የተዛባ ትርክት እንዴት ታሪክን ሊያዛባ እንደሚችል ትልቅ ማሳያ ነው።
ከ2 ሺህ 500 ዓመታት በፊት በግሪኩ የታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶተስ የተሰነዘረው “ግብፅ የዓባይ ስጦታ ናት” የሚለው ብሒል ወንዙን ከምንጩ በማላቀቅ ግብፅን ብቸኛ ባለቤት አድርጎ ለመቅረጽ መሠረት ጥሏል።
ግብፅም ይህን የፈጠራ ትርክት እንደ ፍጹም እውነት ወስዳ፣ ያለ ኢትዮጵያ ፈቃድ ዓባይን በብቸኝነት ጠቅልላ ለመያዝ ራሷን ስታሞኝ ኖራለች። ይህንኑ የተዛባ ትርክት በትውልዶች ቅብብሎሽ ስታስተላልፍም እዚህ ደርሳለች።
ይህ በጥንታዊው ዓለም የተፈጠረው የትርክት መዛባት በሕግ እና በፖለቲካዊ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ በመግባት የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን ለመቅረጽ መንገድ ከፍቷል። በዚህም መሠረት የወንዙ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን መብት የገፈፈው የ1929 የአንግሎ-ግብፅ ስምምነት እና የዓባይን ወንዝ ዓመታዊ ፍሰት ሙሉ በሙሉ በግብፅ እና በሱዳን መካከል ብቻ ያከፋፈለው የ1959 ስምምነት ተፈረሙ። እነዚህ ስምምነቶች ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ያገለሉ እና በወንዟ ላይ ባይተዋር ያደረጓት ነበሩ።
ይህ የተዛባ ትርክት ያስከተለውን ጥልቅ የዲፕሎማሲ ጫና አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት፣ "ላገኘሁት የዓለም መሪ ሁሉ ማስረዳት የሚከብደኝ ‘ዓባይ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ነው' የሚለውን እውነታ ነው" ብለዋል። ይህም የዓለም መሪዎች በአካዳሚክ ምርምሮች እና በመገናኛ ብዙኃን የተመገቡት መረጃ ዓባይን ከግብፅ ጋር ብቻ ያቆራኘ እንደነበር ያሳያል።
ግብፅ የዓባይን ጉዳይ "የሕልውና ሥጋት" አድርጋ ቀርጻዋለች። በዚህም ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ለሚሆነው ሕዝቧ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን ስትገነባ፣ ግብፅ ግንባታውን ለማስተጓጎል ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም። ይህን የምታደርገው ደግሞ የኢትዮጵያን የልማት ጥረትን፣ ቀጣናውን ወደ ቀውስ የሚመራ የደኅንነት ሥጋት አስመስላ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማቅረብ ነው።
ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ የመጠቀም መብቷን በተግባር እንዳታውል የውስጥ ሰላሟን ማወክ ዋነኛው የግብፅ ስትራቴጂ ሆኖ ዘልቋል። ኢትዮጵያ ስለ ዓባይ ውኃ ልማት እንዳታስብ ለማድረግ የውስጥ አለመረጋጋቶችን በገንዘብ እና በሥልጠና መደገፍ፣ እንዲሁም በድንበር አካባቢ ወታደራዊ ውጥረቶችን መፍጠር ሀገራችን ለዘመናት የብጥብጥ እና የድህነት ሰለባ እንድትሆን ታላቅ ዕንቅፋት ሆነው ኖረዋል። የሰሞኑ የግብፅ የአፍሪካ ቀንድ ዙረትም የዚሁ ኋላቀር የቀውስ አዙሪት ስትራቴጂዋ አካል ነው።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተሳካ ሁኔታ መገንባት እና ውኃ መያዝ ለኢትዮጵያውያን የአንድ ፕሮጀክት ስኬት ሳይሆን እውነተኛ ታሪክ ወደ ባለቤቱ የተመለሰበት ታላቅ የብሔራዊ ሉዓላዊነት ማረጋገጫ ነው።
ግብፅ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ባደረገችው ጫና ምክንያት ኢትዮጵያ የውጭ ብድር እንዳታገኝ ተደርጋ የኖረች ቢሆንም፣ ግድቡ በራሳቸው በኢትዮጵያውያን ዐቅም ተገንብቶ የነፃነት ምልክት ለመሆን በቅቷል።
አሁን ላይ ግብፅ እየተከተለችው ያለው የማስፈራራት እና በጎረቤት ሀገራት በኩል አዲስ ጫና የመፍጠር አካሄድ፣ በሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ክፉኛ የተመታውን እና የፈረሰውን የውኃ የበላይነቷን ለመጠገን የሚደረግ ከንቱ ጥረት ነው።
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በዓባይ ላይ የተሰራጨውን የዘመናት የተዛባ ትርክት ከማምከኑም በላይ፣ መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነት በድል አድራጊነት ግዘፍ ነስቶ የቆመበት የትውልዳችን አዲስ ምዕራፍ ነው።
ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን የጋራ ተጠቃሚነትን እና ቀጣናዊ ትብብርን የምትሻ ሲሆን፣ ግብፅ ግን ከቅዠት ዓለሟ ነቅታ አዲሱን እውነት መቀበል ግድ ይላታል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #abay #bluenile #nile #egypt #gerd #ebc

11 days ago