Logo
SeledaPost
በአልጄሪያ በተነሳ የሰደድ እሳት አደጋ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የሐገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የአደጋው መንስኤ በአካባቢው በተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል ነው ተብሏል።

የአልጀሪያ የሐገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ባለፉት ቀናት በተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች የተነሳው ሰደድ እሳት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ገና በቁጥጥር ሥር አልዋለም።

በአደጋው ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የገለጸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ካሣ ለመስጠት የሚያስችል ዝርዝር የጉዳት መጠን እየተጠና መሆኑን አክሏል።

የተነሳው ሰደድ እሳትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በርካታ የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች መሰማራታቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

Seledadotio
Seledadotio
19 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.