Logo
SeledaPost
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የስንዴ እና ማሽላ እርዳታ ላከች

የአሜሪካ መንግሥት ወደ 47,000 ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የምግብ እህል የጫነ የጭነት መርከብ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓዘ መሆኑን አስታውቋል።

በ”ሰላም ለምግብ” መርሃ ግብር የተላከው ይህ እርዳታ 37,700 ቶን ማሽላ እና 9,200 ቶን ስንዴን ያካተተ ነው።

ይህ እርዳታ የተላከው የኢትዮጵያ መንግሥት በስንዴ ምርት ራሱን መቻሉን እና ወደ ውጭ መላክ መጀመሩን በተደጋጋሚ ከገለጸበት ማግስት ነው።

ይሁን እንጂ፣ የአሜሪካ የግብርና መምሪያ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎት በየጊዜው እያደገ በመሆኑ፣ ሀገሪቱ አሁንም ወደ 1.4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የስንዴ ምርት ከውጭ ማስመጣት እንደምትፈልግ ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ በግጭት፣ በመፈናቀል እና በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት አሁንም ከፍተኛ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ይህ የአሜሪካ እርዳታ የሀገሪቱን የስንዴ ራስን የመቻል ጥያቄዎች እና የሰብአዊ ድጋፍ አስፈላጊነትን ዳግም አነጋጋሪ አድርጎታል።

Seledadotio
Seledadotio
18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.