አዲስ ቻምበር ለሜቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
#ethiopia | አንጋፋው የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) የኩባንያ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ለሜቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎችን አበርክቷል።
የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድን ጨምሮ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በማዕከሉ በመገኘት ተጠቃሚዎችን ጎብኝተው ለአገልግሎቱ የሚውሉ ኮምፒዩተሮች፣ የፎቶ ኮፒ ማሽኖች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ምንጣፎች፣ ፋይል ካቢኔቶች፣ ጠረጴዛዎችና ወንበሮችን በእርዳታ መልክ አስረክበዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የተናገሩት የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በመደገፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። እንዲሁም አዲስ ቻምበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ለማዕከሉ የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይም እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
የሜቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል መስራች ዶ/ር ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው፣ አዲስ ቻምበር ለማዕከሉ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ከሚያደርጉ ተቋማት መካከል ቀዳሚ መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በግልም ሆነ ተቋማዊ ደረጃ ለሚያደርጉት ተከታታይ ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
ዶ/ር ቢኒያም አክለውም፣ ወደ ማዕከሉ የሚቀላቀሉ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ፣ እንደ አዲስ ቻምበር ያሉ ተቋማት የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ከ15 ዓመታት በፊት በዶ/ር ቢኒያም በለጠ የተመሰረተው የሜቄዶንያ መርጃ ማዕከል፣ በአሁኑ ወቅት በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች ቅርንጫፎችን በማስፋፋት ለአረጋውያንና ለአዕምሮ ሕሙማን የመጠለያ፣ የእንክብካቤና የሕይወት ድጋፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
አዲስ ቻምበር ላለፉት 79 ዓመታት የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ድምፅ ሆኖ ከንግድ ማህበረሰቡ ጎን በመቆም ከማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎቹም በአንዱ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን መደገፍ ቀጥሏል።

18 days ago