(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከሱዳን እየተስፋፋ የመጣው የእርስ በርስ ግጭት በቀጠናው ላይ የደኅንነት ስጋት እያሳደረ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የሚገኙ ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ወደ ማኅበራዊና ኢኮኖሚው መዋቅር ለማዋሃድ የጀመረችው አዲስ ፕሮጀክት ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀውስ እንደ አዲስ አርአያነት ያለው አማራጭ እየተጠቀሰ ይገኛል። ይሁን እንጂ ይህ ተስፋ ሰጪ እርምጃ እየተራመደ ያለው፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ አሶሳ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ውስጥ የሱዳኑ የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ምስጢራዊ ማሰልጠኛ መክፈታቸውን ተከትሎ በስደተኞች ላይ ከፍተኛ ፍርሃትና ድንጋጤ በነገሰበት ማዕቀፍ ውስጥ መሆኑን የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜታ ጋዜጠኛ ማርክ ታውንሰንድ ከአሶሳ የላከው ዘገባ ያመለክታል።
ከአሶሳ ወታደራዊ ካምፕ ጥቂት ርቀት ላይ በሚገኘው የኡራ ስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚኖሩ 14 ሺህ 500 የሚጠጉ የሱዳን ስደተኞች፣ ከአሰቃቂው የዳርፉር እና የካርቱም ጭፍጨፋ አምልጠው የመጡ ቢሆንም፣ አሁን ደግሞ የሕዋሃት/አር ኤስ ኤፍ ታጣቂዎች በአቅራቢያቸው መገኘታቸው በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ጭምር ሊያድኑንና የባለስልጣናትን የግድያ ዝርዝር ሊያዘጋጁ ይችላሉ በሚል ታላቅ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ የተካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ በድጋሚ ማሸነፋቸውን ተከትሎ፣ የፖለቲካ እና የደኅንነት ተንታኞች የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከታተሉት ይገኛሉ። አንዳንድ ምሁራን አዲሱ የሥልጣን ዘመን አዳዲስ የውስጥና የውጭ ግጭቶችን ሊያስተናግድ ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው ሲሆን፣ በተለይም ኢትዮጵያ በጎረቤት ሱዳን ግጭት ውስጥ ልትገባ የምትችልበት ዕድል ቀውስ ሊፈጥር እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።
ይህ የጂኦ-ፖለቲካዊ ሽኩቻ የሱዳን መደበኛ ጦር፣ የኤርትራ ሰራዊት፣ የትግራይ አማፂያን እና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ባላጋራ የሆነችው ግብፅን በአንድ ወገን አሰልፎ ኢትዮጵያን ሊገጥም የሚችልበትን እጅግ አደገኛና ሁለቱንም ወገኖች ሊያጠፋ የሚችል የክልላዊ ጦርነት ስጋት የደቀነ መሆኑን የገለጸው የዘጋርዲያን ዘገባ፣ ይህ ዓይነቱ መጠነ ሰፊ ውድመት ሊያስከትል የሚችለው ፍርሃት ራሱ በአካባቢው አዲስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ እገዳ ሆኗል የሚሉ ዲፕሎማቶች አሉ።
ነገር ግን ይህ ሁሉ ውጥረት ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግሥት ስደተኞችን በተመለከተ ፍጹም የተለየና ተራማጅ የሆነ ፖሊሲ ይዞ ብቅ ብሏል። መንግሥት በአዲስ አበባው ዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ባዘጋጀው ደማቅ ሥነ-ሥርዓት፣ “ማካተት” የተሰኘ አቅኚ ፕሮጀክትን በይፋ አስጀምሯል። ይህ ስትራቴጂ በአፍሪካ ካሉ ትላልቅ የስደተኞች ቁጥሮች አንዱ የሆነውን የሀገሪቱን ስደተኞች በረድኤት ድርጅቶች ዕርዳታ ላይ ጥገኛ ከማድረግ ይልቅ፣ ወደ ትምህርት፣ ጤና ጥበቃ እና የሥራ ገበታ እንዲገቡ በማድረግ የሀገሪቱ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ አካል፣ እንዲሁም ግብር ከፋይ ነዋሪዎች እንዲሆኑ ታስቦ የተነደፈ ነው። ይህ አሠራር በአሁኑ ወቅት በአሜሪካና በአውሮፓ ከሚታየው ስደተኞችን የመግፋትና ፀረ-ስደተኛ አጀንዳ ፍጹም ተቃራኒ በመሆኑ፣ ለዓለም አቀፉ የስደት ቀውስ አዲስና ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ያምናሉ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) አዲሱ መሪ እና የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዝዳንት የነበሩት ባርሃም ሳሊህ፣ የኢትዮጵያን አካሄድ በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን መፈናቀል ለመፍታት እስካሁን ከተደረጉት ሙከራዎች ሁሉ እጅግ ታላቅና ደፋር እርምጃ ሲሉ አሞካሽተውታል። እሳቸው ራሳቸው የቀድሞ ስደተኛ እንደመሆናቸው መጠን፣ በዓለም ዙሪያ ካሉ 41 ነጥብ 6 ሚሊዮን ስደተኞች መካከል 70 በመቶ ያህሉ ለዓመታት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ተዘግተው እንደሚገኙ ጠቅሰው፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ ፈንድ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ባለበት በዚህ ዘመን ሰዎችን ዘላቂ ባልሆነ ዕርዳታ ላይ ብቻ ጥገኛ ማድረግ እንደማይቻል አስገንዝበዋል። በመሆኑም ምዕራባውያን አገራት ከዚህ ፖለቲካዊ የስደተኞች ጉዳይ ከመሸሽ ይልቅ፣ እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት ስደተኞችን ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያደርግ የአሠራር ዘይቤን መከተልና የስብአዊ መብት አቀራረባቸውን በድጋሚ መተርጎም እንዳለባቸው በጥብቅ አሳስበዋል።

18 days ago