Logo
Getu Temesgen
ቅዱስ ሩፋኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ ምልጃ እና ረድኤቱም አይለየን🙏

ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲሆን፤ “ሩፋ” ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በመጽሐፈ አክሲማሮስ “በራማ ሰማይ የሚገኘውን ሁለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚህም ረቂቅ የሆነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲሆኑ በራማ በሁለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ነገደ መናብርት የሚባሉትን ራማ በሚባለው ሰማይ የሚኖሩትን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ናቸው፡፡ አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ “ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ በሚበርቅ፣ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ” ይላል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚህ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡” ይለናል፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክ 6÷3 ላይም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ተብሏል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም “በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ሁሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚህ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በሆነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ” በማለት አስተምሯል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ፈታሔ ማኀፀን ወሰፋድል። መወለድ መንፈሳዊ። ወሐኪም ሰማያዊ ይባላል። የወላድ ማኀፀን እንዲፈታ በእግዚአብሔር ስለተሾመ አዋላጅ ብትኖርም ባትኖርም ቅዱስ ሩፋኤል በዚያ አይታጣም፡፡ በተለይ በባላገር ያሉ ሴቶች በምጥ ጊዜ ሁሉ መልክአ ሩፋኤል በአንገታቸው ያነግታሉ፣ ይጸልያሉ፣ የተጸለየበትንም ጸበል ይጠጣሉ፤ በፍጥነትም ይወልዳሉ። በየወሩ በ13 ቀን መታሰቢያ በዓሉ የሚከበር ሲሆን ጳጉሜ 3 ደግሞ ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል በረከትና ረድኤቱ አይለየን፤ ምልጃው ይጠብቀን፡፡ ገዳማውያንም ይህን ተራዳኢነቱን በመታመን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፡፡ ገዳማቸውን በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

19 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.