በዱባይ በዜጎች ላይ አሰቃቂ ግፍ ሲፈጽሙ የነበሩ አደገኛ የሰ ዎች አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት፣ በውጭ ሀገር ተደብቀው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ ለገሰ እና ደስታ ተገኝ አበጋዝ የተባሉ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰ ዎች አዘ ዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ወደ ሀገር አስገብቷቸዋል።
የፌደራል ፖሊስ ባደረገው የጋራ ዘመቻ፣ ሁለቱ ዋና ተጠርጣሪዎች 105 ዜጎችን "በተለያዩ ካምፓኒዎች ስራ እናስቀጥራችኋለን’’ በማለት በማታለልና ከ188 ሚሊዮን ብር በላይ ከተጎጂዎች በመሰብሰብ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ ቆይተዋል። ተጠርጣሪዎቹ በዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በደረሰ ጥቆማ መነሻነት ክትትል ሲደረግባቸው የቆየ ሲሆን፣ በቁጥጥር ሥር ውለው ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጥተዋል።
እነዚህ ግለሰቦች ምንም ዓይነት ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው፣ ከአንድ ሰው ከ320,000 እስከ 600,000 ብር በመቀበል በቱሪስት ቪዛ ዱባይ ካስገቡ በኋላ፣ ተጎጂዎችን በተዘጋጀ ክፍል ውስጥ በማገት ለከፍተኛ ረሃብ፣ እንግልትና ጥቃት ሲዳርጉ የነበረ መሆኑ በምርመራ ተረጋግጧል። በተጨማሪም "የመኖሪያ ፍቃድ እናሰጣችኋለን" በሚል ተጨማሪ የገንዘብ ዘረፋ ሲፈጽሙ ቆይተዋል።
በሀገር ውስጥ ሆነው ሰዎችን በመመልመልና የባንክ አካውንት ከፍተው ገንዘብ በማሰባሰብ ሲተባበሩ የነበሩት ብዙአየሁ አውግቸው እና ራህመት አበበ የተባሉ ተባባሪዎቻቸውም በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል። ፖሊስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ከዱባይ የቀጥታ ቨርቹዋል የምስክርነት ቃላቸውን እየተቀበለ ሲሆን፣ ሕጋዊ ሽፋንን በመጠቀም ከሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጋር የሚሰሩ ኤጀንሲዎች ላይም ምርመራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

21 days ago