Logo
EBC
የገጠር ሽግግርን እውን የሚያደርገው የ"ሃሮሜ" መንደር
*****************

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በገጠር ልማት የአርሶ አደሩን አመለካከት በመለወጥ ዘመናዊ ሕይወት እንዲመራ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

በክልሉ የገጠር ሽግግርን እውን ለማድረግ የ"ሃሮሜ" ፕሮግራምን በመጀመር ወደ ሥራ ገብቷል።

የጨፌ ኦሮሚያ አባላት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ደከቦራ ካራና ቱሉ ሬኤ ቀበሌ የሐሮሜ የመንደር ልማትን ጎብኝተዋል።

የጨፌ አባላቱ በጉብኝቱ ወቅት፤ የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ ለማሻሻልና ለመለወጥ በሃሮሜ ቀበሌ የተጀመረው የልማት ሥራ መልካም ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

ሃሮሜ የግንባታ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን፣ በገጠር ሽግግርና በልማት አስተሳሰብ ለውጥ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል።

በሃሮሜ የሚከናወነው የልማት ሥራ የመሠረተ ልማት አቅርቦቶች በአንድ ቦታ ሙሉ በሙሉ እንዲገኙ በማድረግ፣ አርሶ አደሩ ዘመናዊ ሕይወት እንዲኖርና ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ የረዳ መሆኑንም ነው ያነሱት።

ሃሮሜ በዘመናዊ መንገድ የእንስሳትና የሰው መኖሪያን የለየ፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድና ኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ማግኘት መቻሉ የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ በእጅጉ እንደሚቀይር የገልፀዋል።

ሃሮሜ በቀበሌዎች ውስጥ በፕላን ተመስርቶ እየለማ የሚገኝ የገጠር ሽግግር ማእከል ነው።

በሀይማኖት ከበደ

20 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.