#ሰበር ዜና
በዶናልድ ትራምፕ እና በቤንያሚን ኔታንያሁ መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጠረ!
የግጭቱ መነሻ ምንድን ነው?ኔታንያሁ አሜሪካ ዘመናዊ የኤፍ-35 (F-35) ተዋጊ ጄቶችን ለቱርክ ለመሸጥ ወይም ሀገሪቱን በድጋሚ በፕሮግራሙ ውስጥ ለማካተት ያቀደችውን ስምምነት በይፋ መቃወማቸውን ተከትሎ ነው።
ኔታንያሁ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ቱርክ በፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ስር "አስተማማኝ አጋር" አይደለችም በማለት፣ ይህ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የሃይል ሚዛን ያናጋል ሲሉ ዋሽንግተንን አሳስበዋል።
ይህ የኔታንያሁ ይፋዊ ጣልቃ ገብነት በዋይት ሀውስ ውስጥ ከፍተኛ ብስጭት ቀስቅሷል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኔታንያሁ በአሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ውሳኔ ላይ ጣልቃ የመግባት "ምንም መብት የላቸውም" በሚል ክፉኛ መቆጣታቸው ተገልጿል።
የታቀደው ስብሰባ ተሰረዘ?ውጥረቱን ለማርገብ በዋይት ሀውስ ኦቫል ኦፊስ (Oval Office) ይደረጋል ተብሎ ታስቦ የነበረው ፈጣን ስብሰባ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል።
የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ስብሰባው ሊካሄድ እንደነበር ቢዘግቡም፣ የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት ግን ለኔታንያሁ የተያዘ ምንም ዓይነት ይፋዊ ቀጠሮ እንዳልነበረና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ስብሰባውን በራሳቸው ፍላጎት ብቻ ለመፍጠር እየሞከሩ እንደነበር ገልጸዋል።
Seledadotio

21 days ago