(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢቦኒ መፅሄት ‹‹ልእልት ኤሊያና ሮዝ መኮንን አንድ አመት ሞላት›› ብሏል፡፡ በመፅሄቱ ዘገባ መሰረት ይህች ህፃን ዛሬ ጁላይ 17 ቀን የመጀመሪያ ልደቷን እያከበረች ትገኛለች፡፡ ህፃኗ የልእልት ኤድና ተፈሪ መኮንን እና ጀማል ሮቢንሰን ልጅ ናት፡፡ ይህም ማለት የኢትዮጵያ የመጨረሻው ንጉስ አፄ ሀይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ ያደርጋታል፡፡ እናቷ ኤድና የልኡል ራስ ተፈሪ መኮንንና የልእልት አስቴር አብተው ልጅ ናት፡፡
ኤድና ለመፅሄቱ በሰጠችው መግለጫ ‹‹ልጄን ካየሁበት እለት አንስቶ ስሜቴን በቃላት ልገልፀው አልችልም፡፡ የእሷን መምጣት ለረጅም ጊዜ በፀሎት ስንጠባበቅ ነበር›› ያለች ሲሆን ያለፉትን 365 ቀናት መላ ቤተሰቡ ደስተኛ መሆኑን አስረድታለች፡፡ እንደገለፀችውም የኤሊያና ወደዚህ አለም መምጣት ከእሷ ህይወት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ምክንያቱም በወላጆቿ ውስጥ ብቸኛዋ ሴት በመሆኗ ስትወለድ ቤተሰቦቿ በጣም ደስተኛ ለመሆን ችለው ነበር፡፡
እንደዘገባው እናቷ ልእልት አስቴር ወደቤተሰቡ ለተቀላቀለችው የልጅ ልጃቸው ልደት ልዩ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ ይህ ስጦታም ኤድና በህፃንነቷ ስታደርጋቸው የነበሩት ልብሶች ናቸው፡፡ ኤድና ስትናገር ‹‹እናቴ እነዚህን በህፃንነቴ ሳደርጋቸው የነበሩትን ቀሚሶች የት እንዳስቀመጠቻቸው አላውቅም ነበር፡፡ እነዚህን ልብሶች አንዳንዶቹን በቪዲዮ አይቻቸዋለሁ፡፡ ነገር ግን አላስታውሳቸውም›› በማለት ገልፃ በእናቷ ‹‹ሰርፕራይዝ›› መደረጓን አስታውቃለች፡፡

22 days ago