Logo
SeledaPost
ሴት መስሎ በመቅረብ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ የነበረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።

10/11/2018ዓ/ም | በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ሴት መስሎ በመቅረብ ህብረተሰቡን ለመሸወድ እና የተለያየ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር በሜጦማ ቀበሌ ልዩ ስሙ መምህራን መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ታውቋል።

አቡሽ የተባለውና የትውልድ ስፍራው በምዕራብ ባደዋቾ ቆቶ ቀበሌ የሆነው ይህ ግለሰብ ወንድነቱን በመደበቅ ራሱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሴትነት በመለወጥ ህዝብን ሲያታልል እንደነበር ተገልጿል።

ግለሰቡ የወንጀል ዓላማውን ለማሳካት የሴት ቀሚስ ፣ ሰው ሰራሽ ፀጉር (ዊግ) እና የሴት ጡት መያዣ በመጠቀም ራሱን በመለወጥ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ ነበር።

የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር አድማሱ ሱሎሮ እንደገለጹት ግለሰቡ በተደረገበት የህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ጥልቀት ያለው ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

Via፦ ሺንሽቾ መንግስት ኮሙኒኬሽን

Seledadotio
Seledadotio
22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.