Logo
SeledaPost
በቀን 3 ቴምር መብላት ለአእምሮ ጥንካሬና ከአልዛይመር ለመከላከል ፍቱን መፍትሔ _ጥናት

​በሎማ ሊንዳ ዩኒቨርሲቲ (ካሊፎርኒያ፣ አሜሪካ) ተመራማሪዎች የተጠናና በቅርቡ ‘ጆርናል ኦፍ ኒውትሪሽን’ ላይ የታተመ ጥናት እንደሚያመለክተው በቀን ሦስት ቴምር መመገብ ለአእምሮ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ከመሆኑም በላይ የትርሳን (የአልዛይመር) በሽታ የመያዝ ተጋላጭነትን በእጅጉ ይቀንሳል።

ቴምር የአእምሮ ሴሎችን ከጉዳት የሚጠብቁና እብጠትን የሚከላከሉ እንደ ፍላቮኖይድስ እና ፌኖሊክ አሲድ ያሉ አንቲኦክሲዳንቶች እንዲሁም በርካታ ጠቃሚ ቪታሚኖች በውስጡ ይዟል።

​በሳይንሳዊ ምርምሮች መሠረት፣ ቴምር በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩትንና ለአልዛይመር በሽታ መከሰት ዋነኛ መንስኤ የሆኑትን የ"አሚሎይድ ፕላኮች" (amyloid plaques) ክምችት የመከላከል ከፍተኛ አቅም አለው።

​ሆኖም ግን ቴምር ከፍተኛ የካሎሪና የስኳር መጠን ስላለው (በ100 ግራም ውስጥ ወደ 66 ግራም ስኳር ይገኛል)፣ በተለይ የስኳር ህመምተኞች እና የጨጓራ ወይም የአንጀት ችግር ያለባቸው ሰዎች በሚመገቡበት ጊዜ መጠን ማወቅና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ምሁራን ያሳስባሉ።

Seledadotio
Seledadotio
22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.