Logo
SeledaPost
የአጭር ጊዜ ቪዲዮዎች (TikTok እና Reels) ራስን የመቆጣጠር እና የዲሲፕሊን ክህሎትን የሚገነባውን የአንጎል ክፍል ስራ እንደሚያደናቅፉ አዲስ ጥናት አመለከተ

ተጠቃሚዎች በምስሎቹ ቢደሰቱም ባይደሰቱም፥ ቪዲዮዎቹ በአንጎል ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተፅዕኖ አይቀሬ መሆኑ ተረጋግጧል።

​ጥናቱ እንደሚያሳየው፣ እነዚህ ምስል-ወለድ ይዘቶች የተመልካቹን ቀልብ አንዴ ከሳቡ በኋላ ፈጣን የዶፓሚን ሆርሞን መለቀቅን ያስከትላሉ።

ይህም የአንጎልን የተፈጥሮ ውሳኔ ሰጪነት በማደንዘዝ፣ ከዕፅ ሱስ የጠነከረ ከፍተኛ የሱስ የመለከፍ አደጋ ይፈጥራል።

​ይህ የፈጣን መዝናኛ አባዜ የሰውን ልጅ ወደ ማገናዘብ የማይችል “ዞምቢ” እየቀየረው መሆኑን ተመራማሪዎች አስጠንቅቀዋል።

ራስን የመግዛት አቅምን ለመጠበቅ ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መገደብ ወሳኝ እንደሆነም ተመክሯል።

Seledadotio
Seledadotio
23 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.