ኦዲተሮች ላይ ከፍተኛ የስነ-ምግባር ጉድለት እንዳለባቸው ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ባለፉት ሶስት ዓመታት ባደረገው ጥብቅ ማጣራት ፍቃድ በተሰጣቸው ኦዲተሮች እና የሂሳብ ባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ የስነ-ምግባር እና የአቅም ጉድለት እንዳለባቸው ማረጋገጡን አስታውቋል።
የቦርዱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የተመሰከረላቸው ሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፈር ተቋሙ ፈቃድ በሰጣቸው 230 አካባቢ በሚጠጉ ኦዲተሮች ላይ የክትትል ፣ የቁጥጥር እና የጥራት ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ለአሐዱ ተናግረዋል።
በዚህም ባለፉት ሶስት ዓመታት በተሰራው የመፈተሽ ስራ በርካታ ኦዲተሮች ከተቀመጠው መስፈርት የሙያ ደረጃ በታች እየሰሩ መሆናቸው መለየቱን ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም በዘርፉ የሚታየው ችግር ቀላል አለመሆኑን ጠቅሰው ከፍተኛ የሆነ የአቅም ክፍተት እና የስነ-ምግባር ጥሰቶች እንደሚስተዋሉ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ቦርዱ ችግሩ ለታየባቸው ባለሙያዎች የሚወስደው እርምጃ ፤ ቀጥታ ከገበያ ውጣ የሚል የቅጣት ውሳኔን ማሳለፍ ብቻ ሳይሆን ፤ ክፍተታቸውን አውቀው እንዲያርሙ እድል እየሰጠ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
በመሆኑም ኦዲተሮቹ ወደ ሚፈለገው ደረጃ እንዲመጡ የማስተማር ፣ የማሰልጠን እና የማሳወቅ ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
አሐዱ ከፍተኛ የስነ-ምግባር እና የአቅም ጉድለት በተገኘባቸው ኦዲተሮች ላይ የተወሰደ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ አለ ወይ? ብሎ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አቶ ፍቃዱ ፤ ፍቃድ ከመሰረዝ ጀምሮ እስከ 6 ወር የመቅጣት እርምጃ እንደተወሰደ ገልጸው በተጨማሪም በሕግ ሂደት ላይ ያሉ መኖራቸውንም አስታውቀዋል።
በፋሲል አረጋይ

23 days ago