Logo
SeledaPost
የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ታይቶ የማይታወቅ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር እያጠና ነው ተባለ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን የአሜሪካን ወታደራዊ ዘመቻ በከፍተኛ ደረጃ ለማስፋፋት እቅድ እያወጡ መሆኑን የዋሽንግተን የደህንነት ምንጮችን የጠቀሱ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በዋይት ሃውስ እየተመከረባቸው ካሉ አማራጮች መካከል በኢራን ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ እና የኑክሌር ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የአየር ጥቃቶችን ማጠናከር ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህም ባለፈ የትራምፕ አስተዳደር እጅግ አደገኛ ሊባሉ የሚችሉ እና ቀጠናውን ወደ ከፋ ጦርነት ሊከቱ የሚችሉ የጦርነት አማራጮችን እየገመገመ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ ወሳኝ የኢራን ደሴቶችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚገኝበት ተጠቁሟል።

አሜሪካ ጥቃት ልትሰነዝርባቸው ካሰበቻቸው ዋነኛ ኢላማዎች መካከል ዋሽንግተን ከኢራን የኑክሌር መርሃ ግብር ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለው ብላ የምትጠረጥረውና በከፍተኛ ሁኔታ የተመሸገው፣ ከመሬት በታች የሚገኘው "ፒካክስ ማውንቴን" (Pickaxe Mountain) የተባለው ምስጢራዊ ተቋም አንዱ ነው።

ምንም እንኳን የአሜሪካ ጥቃቶች እና የባህር ላይ ወታደራዊ ጫናዎች በኢራን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠናከሩ ቢሄዱም፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እስካሁን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱና አሁንም ቢሆን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚቻልበት የዲፕሎማሲ በር ክፍት መሆኑን በአደባባይ መናገራቸውን ቀጥለዋል።

Seledadotio
Seledadotio
23 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.