በአርቲስት መኮንን ላእከ የመኪና ስጦታ ዙሪያ ኮሚቴው ለዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ጠንካራ ምላሽ ሰጠ
#fastmereja I ለአርቲስት መኮንን ላእከ በሕዝብ ፊት ቃል የተገባለትን መኪና በተመለከተ በዩቶፒያ ቴክኖሎጂ እና በአዘጋጅ ኮሚቴው መካከል ያለው አለመግባባት ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የአርቲስቱ የልደት አዘጋጅ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ አርቲስቱ እስካሁን መኪናውን እንዳልተረከበና ድርጅቱ ከተደረገው የመጀመሪያ መግባባት ውጪ አደገኛ የባንክ ብድርና የውክልና ግዴታዎችን በማምጣቱ ስጦታው ሳይሳካ መቅረቱን በዝርዝር አስታውቋል።
የኮሚቴው መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ መጀመሪያ ላይ ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ለአርቲስቱ መኪና ለመስጠት ኮሚቴው የተወሰነ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ በጠየቀው መሠረት ባለ 1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ በታዋቂው የማስታወቂያ ባለሙያ ዘላለም ኩራባቸው አማካኝነት ተዘጋጅቶ ነበር። ሆኖም ገንዘቡ ከተዘጋጀ በኋላ ድርጅቱን ለማግኘት ኮሚቴው ከአምስት ጊዜ በላይ በአካል ቢሮ ድረስ በመሄድ ጥረት ቢያደርግም ለረጅም ወራት ያገኘው ምላሽ እንዳልነበረ ገልጿል።
ከአምስት ወራት መዘግየት በኋላ ግን ድርጅቱ መኪናውን ለመስጠት አዲስ ሁኔታ ማቅረቡን ኮሚቴው ይፋ አድርጓል። የቀረበው አዲስ ሐሳብ መኪናው በአርቲስት መኮንን ስም በሚወሰድ የባንክ ብድር እንዲገዛ፣ አርቲስቱ ለድርጅቱ ሕጋዊ ውክልና እንዲሰጥ እና ድርጅቱ በተበደረው ገንዘብ እየሠራበት ዕዳውን እንዲከፍል የሚጠይቅ ነው። ይህ አዲስ አካሄድ አርቲስቱን በከፍተኛ ሕጋዊና ፋይናንሳዊ ኃላፊነት ውስጥ የሚጥል በመሆኑ በኮሚቴውና በአርቲስቱ በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
በልደት መድረኩ ላይ የተላለፈው መልዕክት "ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ለአርቲስት መኮንን ላእከ መኪና አበረከተ" የሚል እንጂ ስለ ባንክ ብድር ወይም ስለ ውክልና የተባለ ነገር እንዳልነበረ የጠቀሰው መግለጫው፣ ድርጅቱ የራሱን የማስታወቂያ ፍላጎት ካሳካ በኋላ ቃሉን ለመቀየር መሞከሩ ተገቢ እንዳልሆነ ገልጿል። አርቲስት መኮንን ላእከ በሰይፉ ሾው ላይ ቀርቦ መኪናውን እንዳልተረከበ መናገሩም እውነትን መግለጽ እንጂ ተቋሙን ለማጠላላት የተደረገ እንዳልሆነ ተብራርቷል። ኮሚቴው ከማብራሪያው ጋር በተያያዘ ድርጅቱ እንዲፈረም የጠየቀውን የውክልና ሰነድ ናሙና ለሕዝብ እይታ ያያዘ ሲሆን፣ በሕዝብ ፊት የተገባ ቃል በማስታወቂያ መሣሪያነት ብቻ ሳይሆን በታማኝነትና በተግባር ሊፈጸም እንደሚገባ አሳስቧል።
ፎቶ ፎከስ ስቱዲዮ

24 days ago