Logo
FastMereja
ዛሬ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ደማቅ ቀን ነው። አድማጮች በሙዚቃው የሚወዱት፣ ግጥምና ዜማውን በራሱ የሚቃኘው ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የተወለደበት ቀን ነው።

​የትውልድ እና እድገቱ አዲስ አበባ የሆነው ቴዲ፣ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርቱን የተከታተለውም እዚሁ ከተማ ነው። ለሙዚቃ ባለው ከፍተኛ ፍቅር እና ባሳየው የፈጠራ ብቃት፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ስሙ በጉልህ እንዲሰፍር አድርጎታል።

​"ፍቅር ያሸንፋል" በሚለው አባባሉ የሚታወቀውና በአድናቂዎቹ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ቴዲ፣ ከውጫዊ ተጽዕኖዎች ይልቅ ትኩረቱን ሙዚቃው ላይ ብቻ በማድረግ ለሙዚቃው ኢንዱስትሪ ትልቅ አሻራ ጥሏል።

​ዛሬ የተወለድክበት ቀን ነውና፣ ለቀጣይ የኪነ-ጥበብ ስራዎችህ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን። እንኳን ተወለድክ!

24 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.