Logo
SeledaPost
ትራምፕ፡ "የአሊ ኻሜኒ ልጅ 90 በመቶ ሰውነቱ ተዳክሟል "

​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በቅርቡ በተገደሉት የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ ምትክ ስልጣን የያዙት ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ "90 በመቶ ሰውነታቸው ተዳክሟል " ሲሉ ተናገሩ።

​ትራምፕ የኢራን ወታደራዊ መሪዎች መገደላቸውንና የአገሪቱ የጦር መዋቅር፣ የአየርና የባህር ኃይል ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።

ሞጅታባ ኻሜኒ በየካቲት 21ዱ የአሜሪካና እስራኤል ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ በአደባባይ አልታዩም።

​በኻሜኒ ቀብር ላይ ጥቁር ማስክ አድርጎ የታየው ግለሰብ የሞጅታባ ልጅ መሀመድ ጃቫድ መሆኑ ታውቋል።

እርሱም በሳንሱር ጥቃቱ ከባድ የፊት ቃጠሎና ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።

Seledadotio
Seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.