Logo
YenetaTube
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የብድር ጣሪያን ማንሳቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ከዚህ ቀደም በባንኮች ላይ ጥሎት የነበረውን ጊዜያዊ የብድር ጣሪያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን ገልጿል። ይህ ውሳኔ ወደ ገበያ መር የገንዘብ ፖሊሲ ስርዓት ለመሸጋገር የተወሰደ እርምጃ መሆኑ ተጠቅሷል።

የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ባንኩ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔን በአንድ በመቶ ከፍ አድርጓል። በተጨማሪም የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል የሚያስችል አዲስ የታለመ የመጠባበቂያ ግዴታ ማዕቀፍ አስተዋውቋል።

ከውጭ ንግድ ጋር በተያያዘም ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ኮሚሽንን ከ2.5 በመቶ ወደ 1.5 በመቶ ዝቅ አድርጓል። እንዲሁም ላኪዎች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ለባንክ የመሸጥ ግዴታ (Surrender requirement) ከ50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ በማድረግ፣ የላኪዎችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና የውጭ ምንዛሪ ገበያውን ለማጠናከር አቅዷል።

26 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.