"ባለፉት አምስት ዓመታት ከ98 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ ለቆጣቢዎች ተላልፈዋል"— ከንቲባ አዳነች አቤቤ
26 ሺህ 563 የመንግስት ቤቶችም ለልማት ተነሺዎች እንዲተላለፉ ተደርጓል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት በቤት ልማት ዘርፍ ያስመዘገባቸውን ውጤቶችና በቀጣይ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አስመልክቶ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ ሰፊ ሪፖርት አቅርበዋል።
ከንቲባዋ በሪፖርታቸው እንዳመለከቱት፣ የቤት ጥያቄ መሰረታዊና አንገብጋቢ የሕዝብ ጥያቄ መሆኑን በመረዳት ባለፉት አምስት ዓመታት በመንግስት፣ በሪል እስቴት፣ በህብረት ስራ ማህበራትና በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት በጠቅላላው 496 ሺህ 971 ቤቶች ተገንብተዋል።
በተለይም ለቤት ፈላጊው ማህበረሰብ ትልቅ ተስፋ የሆነውን የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ በተመለከተ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ98 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ ለቆጣቢዎች ተላልፈዋል። ከዚህ በተጨማሪም 26 ሺህ 563 የመንግስት ቤቶች ለልማት ተነሺዎች እንዲተላለፉ ተደርጓል።
በአሁኑ ወቅትም የመንግስት ቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ የግንባታ አማራጮች የ179 ሺህ 516 ቤቶች ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ከንቲባዋ ገልጸዋል። ከመንግስት በጀት ብቻ ለተገነቡ ቤቶች አፈጻጸሙ ከ40 በመቶ በላይ መድረሱንም ጠቁመዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በቤት ልማት ዘርፍ የነበረበትን ከፍተኛ የዕዳ ጫና በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ከዚህ ቀደም ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሶ የነበረው የባንክ ብድርና ወለድ፣ በከፍተኛ ጥረት 62 ቢሊዮን ብር መክፈል በመቻሉ አሁን ላይ ቀሪው ዕዳ ወደ 37 ቢሊዮን ብር ዝቅ ማለቱን ከንቲባዋ አስረድተዋል።
ለዓለም አሰፋ

27 days ago