(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እ.ኤ.አ በ2030 በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ሀገራትን ቁጥር ወደ 64 ለማሳደግ ያቀረበው ሀሳብ ከወዲሁ ከፍተኛ ተቃውሞ እና ትችት እያስተናገደ ይገኛል።
የውድድሩን የማጣሪያ ሂደት ትርጉም አልባ ያደርገዋል በሚል በስፋት የተተቸው ይህ ዕቅድ፣ በተለይም በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ቼፈሪን ዘንድ "መጥፎ ሀሳብ" የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ቼፈሪን ሀሳቡ ውድድሩንም ሆነ የአውሮፓን የማጣሪያ ውድድሮች በእጅጉ እንደሚጎዳ ተናግረዋል። የሰሜን አሜሪካው ፕሬዝዳንት ቪክቶር ሞንታግሊያኒም በተመሳሳይ ውሳኔውን "ጥሩ ሀሳብ አይደለም" ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ባለው የ48 ሀገራት ውድድር ላይ የጋና ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ካርሎስ ኬይሮዝ የቡድን ድልድል ጨዋታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ፣ የቡድኖች ቁጥር መጨመር የማጣሪያውን ሂደት ዋጋ እንዳሳጣውና ውድድሩን "ተራ እና ዝቅተኛ" እንዳደረገው በቁጭት ገልጸዋል። ከፊፋ 210 አባል ሀገራት መካከል ከሩቡ በላይ የሚሆኑትን በአንድ ውድድር ላይ ማሳተፍ፣ የክልላዊ ማጣሪያዎችን ፉክክር ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል የሚለው ስጋት የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል።
እነዚህ ሁሉ ጠንካራ ተቃውሞዎች ቢኖሩም፣ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ግን ከዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በኋላ ይህ የ64 ሀገራት ተሳትፎ ጉዳይ በሚመለከታቸው ኮሚቴዎች በቁምነገር እንደሚታይ አረጋግጠዋል። ኢንፋንቲኖ "እያንዳንዱ ሀገር በዓለም ዋንጫው የመሳተፍ ህልም እንዲኖረው ሊፈቀድለት ይገባል፤ ለትናንሽ ሀገራት እድል ካልሰጠን ራሳቸውን ለማሻሻል የሚያስችል መነሳሳት አይኖራቸውም" በማለት ዕቅዱን ተከላከለዋል። ዘንድሮ ወደ 48 ያደገውን ውድድርም "100 በመቶ ስኬታማ" ሲሉ አሞካሽተውታል።
ይህ የ64 ሀገራት ውድድር ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የመነጨው በደቡብ አሜሪካ የእግር ኳስ ባለስልጣናት ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በ2030 ውድድር ላይ ያላቸውን የማስተናገድ ሚና ለማሳደግ ነው። የ2030 የዓለም ዋንጫ በሶስት አህጉራት እና በስድስት ሀገራት (ሞሮኮ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን እንዲሁም በደቡብ አሜሪካ ኡራጓይ፣ አርጀንቲና እና ፓራጓይ) የሚካሄድ ሲሆን፣ በአሁኑ ድልድል የደቡብ አሜሪካ ሀገራቱ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ጨዋታ ብቻ እንዲያስተናግዱ ነው የተወሰነው። ሀገራቱን ወደ 64 በማሳደግ ግን እያንዳንዳቸው ሙሉ የምድብ ጨዋታዎችን ማስተናገድ ይችላሉ የሚል እሳቤ አላቸው። የኮንሜቦል ፕሬዝዳንት አሌሃንድሮ ዶሚንጌዝ ይህንን ሀሳብ "ዓለምን ቢያንስ ለአንድ ጊዜ አንድ የሚያደርግ ህልሜ ነው" ብለውታል።
የዓለም ዋንጫው ከ1998 እስከ 2022 ድረስ በ32 ሀገራት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የ2026 የዓለም ዋንጫ ተሳታፊዎቹ ወደ 48 ማደጋቸው ይታወቃል።
በሌላ ዜና የፊፋው ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር "በየቀኑ ማለት ይቻላል" እየተነጋገሩ መሆኑን እና ትራምፕ እስካሁን በአካል ተገኝተው ጨዋታ ባይመለከቱም በቴሌቪዥን እያንዳንዱን ጨዋታ እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዓለም ዋንጫው የፍጻሜ ጨዋታ ላይ በአካል ታድመው ለአሸናፊው ቡድን ታላቁን ዋንጫ እንደሚያበረክቱም ኢንፋንቲኖ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

26 days ago