የከተማ ግብርና፡ ለዘላቂ የምግብ ዋስትናና ከተማ ልማት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዙሪያ የከተሞች መስፋፋት፣ የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የምግብ ዋጋ መናር እና የአየር ንብረት ለውጥ በምግብ ሥርዓት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ የከተማ ግብርና የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ አካባቢን ለማሻሻል እና የከተማ ነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ከሚያገለግሉ አስፈላጊ አማራጮች አንዱ ሆኗል።
የከተማ ግብርና በከተሞች ወይም በከተማ ዳርቻዎች ውስጥ የሚከናወን የሰብል ልማት፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርት፣ የእንስሳት እርባታ፣ የዶሮ እርባታ፣ የንብ ማነብና ሌሎች የግብርና ተግባራትን የሚያካትት የምርት ሥርዓት ነው።
ይህ ግብርና በጓሮ፣ በቤት ጣሪያ፣ በትንሽ ክፍት ቦታዎች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በተቋማት ግቢዎች እና በማህበረሰብ የጋራ መሬቶች ላይ ሊካሄድ ይችላል።
በኢትዮጵያ የከተማ ግብርና በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ሲሆን፤ የከተማ ነዋሪዎች በጓሮ አትክልት ልማት፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት ላሞች እርባታ፣ በንብ ማነብ እና በተለያዩ የግብርና ስራዎች ላይ በስፋት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የመንግሥት ተቋማት እና የልማት አጋሮች የሥልጠና፣ የግብዓት ድጋፍ እና የቴክኒክ ምክር በመስጠት ዘርፉን ለማጠናከር ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ ነው።
በኢትዮጵያ የከተማ ግብርናን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እንደ ግሪን ሃውስ፣ የውኃ ቆጣቢ የመስኖ ዘዴዎች፣ የጣሪያ አትክልት ልማት እና ቋሚ የምርት ሥርዓቶች በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ማጠናከር ይቻላል።
ይህም የከተሞችን ኢኮኖሚ ከማጠናከር ባሻገር ለዘላቂ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
የከተማ ግብርና ምግብን ለማምረት ብቻ ሳይሆን የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ ገቢን የሚያሳድግ፣ አካባቢን የሚያሻሽል እና የከተማ ነዋሪዎችን የሕይወት ጥራት የሚያሻሽል ዘርፍ ነው።
በኢትዮጵያም የዘርፉ አቅም ከፍተኛ በመሆኑ የመንግሥት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የምርምር ተቋማት እና የማህበረሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ ከተጠናከረ የከተሞቻችንን የምግብ ዋስትናና የኢኮኖሚ እድገት በከፍተኛ ደረጃ ማጎልበት ይቻላል።
የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በከተማና በገጠር መተግበር መጀመሩ በከተሞች ያለውን የግብርና ስራ ለማሳደግ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። በተለይም በወተት ላሞች፣ በዶሮ፣ በዓሣ እና ንብ ማነብ ከዝርያ ማሻሻል ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎች በትኩረት መሰጠታቸው የከተማ ግብርናን ውጤታማ ለማድረግ አግዟል።
በአመለወርቅ ደምሰው

27 days ago