የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር የአምቡላንስ እና የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
#fastmereja | የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር የአምቡላንስ መኪና እና የ2 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ። ድጋፉ የተከናወነው በየዓመቱ ሐምሌ 4 ቀን ለታቀደው የመቄዶንያ ጉብኝት እና ድጋፍ መርሃ ግብር አካል ነው።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ ባንድ እና ኦርኬስትራ እንዲሁም የብዙሃን መገናኛ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት መቄዶንያን በመደገፍ ላይ ሲሆን፣ የዘንድሮው ስጦታ የአምቡላንስ መኪና እና የገንዘብ ድጋፉን ያካተተ ነው። የተበረከተው አምቡላንስ አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ለመስጠት፣ የህይወት አድን ስራዎችን ለማከናወን እና የከፋ የጤና ጉዳትን ለመከላከል ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው በስፍራው ተገልጿል።
የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች ዶክተር ብንያም በለጠ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማህበሩ የሚሰጠው የሞራል እና የስነ-ልቦና ጥንካሬ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የፖሊስ ተቋም የሚያሳየው ይህ የሰብዓዊነት እሴት ለሌሎችም ተቋማት አርአያ የሚሆን መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ብንያም፣ ድጋፉ ማህበራዊ ሰላምን እና በጋራ ችግሮችን የመፍታት ባህልን እንደሚያጠናክር አስገንዝበዋል።
ማህበሩ እየገነባ ያለውን ግዙፍ ህንፃ እና በክልል ከተሞች በመካሄድ ላይ ያሉ ግንባታዎችን በተመለከተ የገለጹት መስራቹ፣ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የምረቃ ፕሮግራም እንደሚኖር አስታውቀዋል። በዕለቱ የተገኘው የፖሊስ አመራር እና ሌሎች አካላት በቦታው ተገኝተው ድጋፍ ማድረጋቸው ለሰብአዊ ስራዎች ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተመላክቷል።

28 days ago