Logo
EBC
ሀገራዊ ምክክሩ የዜጎችን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል - የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች
*********************

የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላምና የሕዝቦችን ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ታቅዶ በተለያዩ ስልታዊ ምዕራፎች ሲካሄድ የቆየው ሀገራዊ ምክክር፤ ከመጪው ሐምሌ 8 ጀምሮ ታሪካዊውን የምክክር ጉባኤ ያካሂዳል፡፡

የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች በዚሁ ጉዳይ ላይ ለኢቲቪ በሰጡት አስተያየት፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው የዜጎችን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ታላቅ ሀገራዊ መድረክ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም፣ የሕዝቦችን የዘመን አይሽሬ ፍቅር፣ አንድነትና መተሳሰብ ይበልጥ ሊያጠናክሩና ሊያጎለብቱ የሚችሉ መሠረታዊ ምክረ-ሐሳቦችን በከፍተኛ ጉጉት እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል።

ይህ ታሪካዊ የምክክር ጉባኤ ከምንም በላይ በሀገሪቱ አስተማማኝና ፍጹም ሰላምን በመፍጠር፣ በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተከናወኑ የሚገኙ ታላላቅ ሀገራዊ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል ብስለት የተሞላበት ውይይት እንደሚያስተናግድ ነዋሪዎቹ ጠቁመው፤ ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ከፍታና የሚያሻግሩ ብሔራዊ መፍትሔዎች እንደሚገኙበት ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወክለው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ የሚመካከሩ የጉባኤው አባላት በሙሉ፣ በውይይቱ ወቅት ንቁና የበሰለ ተሳትፎ በማድረግ የተጣለባቸውን ታሪካዊና ትውልዳዊ ሀገራዊ ኃላፊነት በታማኝነት ሊወጡ እንደሚገባም ነዋሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

በጀማል አህመድ
#ebc #ethiopia #assosa #nationaldialogue

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.