Logo
EBC
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፖለቲካ ዙሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች፡-
**********************

👉🏽ላለፉት አምስት ዓመታት በምክር ቤቱ ውስጥ የሕዝብን እና የፓርቲያቸውን ድምጽ ሲያሰሙ ለነበሩ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት (እንደ ኢዜማ፣ አብን እና ሌሎችም) እንዲሁም ለብልጽግና አባላት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

👉🏽በዘንድሮው ምርጫ ምክንያት ወደ ምክር ቤት ለማይመለሱ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት፣ የመንግሥት ፍላጎት በጋራ መሥራት መሆኑን በመግለጽ፤ ከምክር ቤት ውጭም ቢሆን ሀገርን ለማልማት ከመንግሥት ጋር አብረው እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

👉🏽የዘንድሮው ምርጫ ከተለመደው የፖለቲካ ፉክክር ባለፈ፣ ራሱ ምርጫው እንዳይካሄድ በ"ባንዳዎች" እና ፀረ-ምርጫ ኃይሎች ከፍተኛ ጫና እና ማሸማቀቅ እንደነበረበት አንስተዋል።

👉🏽ሕዝቡ ማስፈራሪያዎችን ወደጎን በመተው ሌሊት ወጥቶ በመሰለፍ ድምፁን መስጠቱን፤ በዚህም ፅንፈኝነትን፣ ባንዳነትን እና ዘረኝነትን እንደማይፈልግ በአንድ ድምፅ ማሳየቱን ገልጸዋል።

👉🏽ሕዝቡ ለመንግሥት ጅምር ሥራዎች ዕውቅና በመስጠት ድምፁን ቢሰጥም፣ ይህ ድምጽ "ባዶ ቼክ" መሆኑን አሳስበዋል።

👉🏽ሕዝቡ ሥርአታዊ ሌብነት (ሙስና) እንዲጠፋ እና አገልግሎት እንዲሻሻል አደራ መስጠቱን፤ ይህን አደራ መንግሥት በአግባቡ ካልተወጣ፣ ጥይት ሳይፈራ የመረጠው ሕዝብ በተመሳሳይ ድፍረት የተቃውሞ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

👉🏽ብልጽግና ፓርቲ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሲል፣ 15 በመቶ የሚሆነውን የምክር ቤት ወንበር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ብቻቸውን እንዲወዳደሩበት ማድረጉን እና ይህም በርካታ ፓርቲዎች ፓርላማ እንዲገቡ ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል።

👉🏽በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ብልጽግና ፓርቲ ይዞት ከሚቀርባቸው አጀንዳዎች አንዱ፣ በሥልጣን ላይ ያለ መንግሥት (መሪ) ከሁለት የምርጫ ዘመን በላይ መቆየት የለበትም የሚል የሕገ-መንግስት ማሻሻያ ሀሳብ መሆኑን አስታውቀዋል።

👉🏽ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው ከ225 በላይ፣ ፓርቲው ደግሞ ከ4 ሺህ በላይ የሕዝብ መድረኮችን ማካሄዱን፤ እንዲሁም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሕዝብ ውይይቶችን በስፋት እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

👉🏽ታፍነው የቆዩ ብሶቶች በነጻነት እንዲወጡ በመደረጉ፣ ብሔርን ከብሔር እና ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ የሕዝብ ለህዝብ ግጭቶች በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሳቸውን ገልጸዋል።

👉🏽አሁን የሚታዩት ግጭቶች የሕዝብ ለሕዝብ ሳይሆኑ፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ በሚፈልጉ ኃይሎች የሚደገፉ "ሽፍቶች እና ባንዳዎች" የሚፈጥሩት መሆኑን ገልጸዋል። የፀጥታ ተቋማት (Law Enforcement Agencies) በሰው ኃይልም ሆነ በቴክኖሎጂ አቅማቸውን እያሳደጉ መሆኑን አረጋግጠዋል።

👉🏽በኦሮሚያም ሆነ በአማራ ክልል ያሉ የታጠቁ ኃይሎች ግጭት ወደ ድል ስለማያደርስ፣ ውይይት እና ድርድርን መርጠው ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱና በጋራ ሀገር እንዲገነቡ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።
#ethiopia #parliament #pmabiyahmed #politics #ebc

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.