Logo
SeledaPost
በቀጣይ 5 ዓመታት 1.5 ሚሊዮን ቤቶች ይገነባሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በቀጣይ አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ማብራሪያ ባለፉት ሰባት ዓመታት 1.2 ሚሊዮን ቤቶች መገንባታቸውን ጠቅሰው በቀጣዩ አምስት ዓመታት ተጨማሪ 1.5 ሚሊዮን ቤቶች እንደሚገነቡ ተናግረዋል።

እንደ ገለጻቸው  የቤቶቹ ግንባታ በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ ተሳትፎ እና በሌሎች የአጋርነት መንገዶች የሚከናወን ሲሆን ለዚህም የሚያግዝ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ በካቢኔ መፅደቁን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የኮንስትራክሽን ግብዓት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ምርት መጀመራቸውን፣ዘርፉን የሚደግፉ የሰው ኃይል ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን እና በከተማና በገጠር የቤት ግንባታ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የቤት ፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ የሞርጌጅ ስርዓት እየተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመው፣ ዜጎች ቤት በቀጥታ መግዛት ባይችሉም በረጅም ጊዜ ክፍያ ከገቢያቸው ጋር በሚጣጣም መንገድ ባለቤት እንዲሆኑ መንግሥት በተለያዩ አማራጮች ላይ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.