Logo
Getu Temesgen
"የክርስቶስን ሥጋና ደም በተቀበለ አፌ አልዘፍንም!"
#ethiopia | ድምጻዊት ራሔል ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዓቷ ዛሬ በክብር የተፈጸመ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይልና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በሥነ ሥርዓቱ በመሳተፍ የመጨረሻ ሽኝት አድርገውላታል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙ በርካታ አድናቂዎችና ወዳጆቿ፣ ለሀገርና ለሙዚቃ ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በማስታወስ ክብራቸውን ገልጸዋል።

ራሔል ዮሐንስ በአንድ ወቅት በቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ ላይ እንድትዘፍን በተጠየቀችበት ጊዜ፣ "የክርስቶስን ሥጋና ደም በተቀበለ አፌ አልዘፍንም" በማለት የሰጠችው ምላሽ በብዙዎች ዘንድ ሲታወስ ቆይቷል።

ቤተሰቦቿ፣ ወዳጆቿና አድናቂዎቿ ለሟቿ የመጨረሻ ስንብት ሲያደርጉ፣ በእምነቷ ጸንታ የኖረች እና በሕይወቷ ያስቀመጠችው መንፈሳዊ አቋም የሚታወስ መሆኑን ገልጸዋል።

ድምጻዊቷ በአከበረችው የቃል ኪዳን ቤተ ክርስቲያን አጸድ ውስጥ በክብር ተቀብራለች።

ነፍሷን ይማር።

እስክንድር መርኀጽድቅ

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.