ሰላም! እንደምን አደራችሁ?
የኮሪደር ልማት...ከከተማ እስከ ገጠር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በስፋት እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በጥቂት ዓመታት ውስጥ የከተሞችና የገጠራማ አካባቢዎችን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት በከፍተኛ ደረጃ እያሻሻለ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት እንዳሉት፥ ከተሜነት በዕቅድና በእውቀት ካልተመራ ከተሞች ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡
ለዚህም ነባሩን የዘፈቀደ አሠራር በማስቀረት ነገን ታሳቢ ያደረገና ሁሉን አቀፍ ብልጽግናን የሚያረጋገጥ የኮሪደር ልማት ሥራ በስፋት እያተተገበረ መሆኑን ተናግረዋል።
አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ከተሞች የተመሠረቱት በጦር ካምፕነት እንጂ በተጠና ማስተር ፕላን ባለመሆኑ ከተሞቹ እያደጉ በሚመጡበት ወቅት በርካታ ችግሮች እያጋጠማቸው ይገኛል።
አሁን ላይ እየተከናወነ ያለው የከተማ ኮሪደር ልማት ይህንን እቅድ አልባ ጉዞ በመቀየር ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ ለአብነትም በመዲናዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹና ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች እጅግ ማራኪ አድርገዋታል።
ይህ ጅማሮ የሀገሪቱን የኮንፈረንስ ቱሪዝም አድማስ በከፍተኛ ደረጃ በማስፋት በዚህ በጀት ዓመት ብቻ ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን የውጭ ጎብኚዎችን ማስተናገድ አስችሏል።
በዚሁ ጊዜ ውስጥ በቱሪዝም ፍሰት ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የቱሪዝም ማዕከል በዓለም ፈጣን የቱሪዝም ዕድገት እያሳዩ ካሉ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ የኮሪደር ልማት ስራዎች ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
አሁን ላይ አስደናቂ ውጤት እያስመዘገበ የሚገኘውና በከተማ የተጀመረው ስኬታማ የኮሪደር ልማት ተሞክሮ ወደ ገጠር በመስፋፋት የአርሶና አርብቶ አደሩን የአኗኗር ዘዬ እያሻሻለ ይገኛል።
የገጠር ኮሪደር ሀገራዊ ልማት ዋና ዓላማ የእያንዳንዱን አርሶ እና አርብቶ አደር አኗኗር በማሻሻል እንደ ሀገር የሚታሰበውን ብልጽግና ማረጋገጥ ነው።
በተጨማሪም የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር በማዘመን ከተማ ሄደው የሚያገኟቸውን መሠረታዊ አገልግሎቶች ባሉበት አካባቢ እንዲያገኙ ማድረግ የኮሪደር ልማት ግብ ነው።
ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች፣ በባሕላዊ የግንባታ ዘዴ፣ በተደራጀ ዕቅድና በህብረተሰብ ንቁ ተሳትፎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተገነቡት ሞዴል የገጠር መንደሮች ለየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የተሻሻለ የአኗኗር ዘይቤ ጠንካራ እድል ፈጥረዋል።
ለአብነትም ሀማሳ፣ ጎሮ ወረዳ፣ ሀረሪ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ጉራፈርዳ እንዲሁም በሀላባ፣ ከምባታ፣ ሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡና በሀገር ደረጃ እንደ ተሞክሮ ሊወሰዱ የሚችሉ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎችን መጥቀስ ይቻላል።
የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከተማን ከማስዋብና ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ የገጠሩን ማህበረሰብ የኑሮ ደረጃ ወደ ላቀ ምዕራፍ በማሸጋገር ሁለንተናዊ የብልጽግና መሣሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።
በአነስተኛ ወጪና የአካባቢን የተፈጥሮ ጸጋ በመጠቀም የእያንዳንዱን ዜጋ ሕይወት አኗኗር መቀየር እንደሚቻል በተግባር የታየበትን ይህንን ልማት አጠናክሮ ማስቀጠል ለዘላቂ ሀገራዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

1 month ago