ኢራንና አሜሪካ በዶሀ የነበራቸው ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ቀነሰ
ዩኤስ እና ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ትኩረት አድርገው የነበረበት የዶሃው ውይይት መጠናቀቁን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ለተከታታይ ሶስት ቀናት መቀነሱን አለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት ይገኛሉ።
ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ዙሪያ ባደረጉት ንግግር ላይ መሻሻል ማሳየታቸውን ኳታር ማስታወቋን ተከትሎ ነው የአቅርቦት መቋረጥ ስጋት በመቀነሱ የነዳጅ ዋጋ ሐሙስ ዕለት ለሶስተኛ ተከታታይ ቀን የቀነሰው።
የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ የወደፊት ዋጋ በ66 ሳንቲም ወይም በ0.92 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ በባሬል 70.91 ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት ደግሞ በ59 ሳንቲም ወይም በ0.86 በመቶ በመቀነስ በባሬል 67.99 ዶላር ሆኗል። ይህም ካለፈው የካቲት 27 ጀምሮ የታየው ዝቅተኛው የዋጋ ደረጃ ነው ሲል ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል።
የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በኤክስ ማህበራዊ ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ንግግሩ በሰኔ ወር ጦርነቱን ባቆመው የመግባቢያ ሰነድ ላይ ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ "አዎንታዊ መሻሻል" አሳይቷል ማለታቸውን ነው የተነገረው።
ሮይተርስ ባስነበበው ዘገባ እንዳለው ሁለቱ ወገኖች ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መሻሻል ማሳየታቸውን የሚጠቁም ምንም ምልክት እስካሁን አልታየም።
በኢራን እና በዩኤስ ተደራዳሪዎች መካከል የሚቀጥለው ስብሰባ ከሐምሌ 9 በኋላ የሚካሄድ ሲሆን ይህም በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት የኢራኑ ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ ከሚደረገው የቀብር ሥነ ሥርዓት በኋላ መሆኑን የኳታሩ ሚኒስቴር አክሎ ገልጿል።
ኢራን በባህር ወሽመጥ ላይ ያላትን ቁጥጥር እና ወደ ባሕረ ሰላጤው በሚገቡ ወይም በሚወጡ መርከቦች ላይ ክፍያ የመጣል አቅሟን በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ለማግኘት ቆርጣ የተነሳች መሆኗን ሁለት ከፍተኛ የኢራን ምንጮች ገልጸዋል። ይህንን ግብ ለማሳካት አስፈላጊ ከሆነ ኃይል የመጠቀም ፍላጎት እንዳላትም ጠቁመዋል።
ሀናን ሸምሱ

1 month ago