ፀደቀ‼️
የታክስ ቅሬታ አጣሪው ተቀየረ፤ የታክስ ቅጣትም በግማሽ ተቀነሰ‼️
*ሰኔ 23/2018 ዓ/ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ላይ ጠቃሚ ማሻሻያዎችን አድርጎ በትናንትናው ዕለት አጽድቋል። ማሻሻያው በተለይም ለታክስ ከፋይ ተቋማት የፍትህ አድማሱን የሚያሰፋና የቅጣት ጫናን የሚቀንስ ነው።
በአዋጁ የተካተቱት ዋና ዋና ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፦
ከዚህ ቀደም በታክስ ባለሥልጣኑ በራሱ ይሰየም የነበረው የታክስ "አስማሚ" (Mediator)፣ ከአሁን በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚሰየም ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን ይተካል፡፡ ይህም የታክስ ክርክሮች ፍትሃዊ እና ገለልተኛ በሆነ መንገድ እንዲታዩ ያስችላል።
ታክስ ከፋዮች በታክስ አወሳሰን ወቅት ያልቀረቡ ነገር ግን በኋላ ላይ የዕዳ መጠን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ማስረጃዎችን ሲያቀርቡ ይጠብቃቸው የነበረው 20 በመቶ ቅጣት፣ በግማሽ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
የታክስ ህግን በመተላለፍ ወንጀል የሚፈጽሙ ድርጅቶች ላይ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ድንጋጌ ተካቷል። በዚህም መሰረት ወንጀሉ በተፈጸመበት ወቅት በስልጣን ላይ የነበሩ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጆች ወይም የፋይናንስ ኃላፊዎች ለወንጀሉ በግል ተጠያቂ እንደሚሆኑ ህጉ በግልጽ አስቀምጧል።
ይህ ማሻሻያ የታክስ አስተዳደርን ይበልጥ ግልጽ፣ ፍትሃዊ እና ተጠያቂነት ያለው ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

1 month ago