ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን መረቁ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት መርቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ይህ ሰፊ መሰረተ ልማት የወንዝ መከላከያ ግንቦችን፣ ዘመናዊ ድልድዮችን እና ሰፊ አረንጓዴ ስፍራዎችን በጋራ የያዘ ነው ብለዋል።
በዛሬው ዕለት የተመረቀው ፕሮጀክት 87 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን ÷ 10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዳለው አመልክተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የግንባታ ስኬት ብቻ ሳይሆን መዲናዋን የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋምና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች፣ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስልታዊ ሽግግር የሚያፋጥን ታላቅ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
1 month ago