ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ የቀድሞ ህወሓት ቡድን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየፈጸመ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ ህወሓት ቡድን ተፈናቃይ አይመለስም በማለት በህዝብ ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየፈጸመ ነው አሉ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አታክልቲ ኃ/ስላሴ።
አቶ አታክልቲ ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ቡድኑ ከትግራይ ህዝብ ጥቅም ይልቅ የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል ከጥፋቱ የማይመለስ ጸረ ሰላም ኃይል ነው ብለዋል፡፡
ቡድኑ በትግራይ ክልል ሠላም እንዲመጣ ልማት እንዲረጋገጥ፣ ዴሞክራሲ እንዲሰፍንና ሕዝቡ ተረጋግቶ እንዲኖር የማይፈቅድ የጥፋት መልዕከተኛ ነው ሲሉም የቡድኑን ክፋት አብራርተዋል።
የቡድኑ አመራሮች ይህንን የጭካኔ ተግባር ከአብራኩ በወጡበት ሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትም የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ነው ብለዋል።
ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ተልዕኮ ተቀብሎ ትግራይን የጦርነት አውድማ በማድረግ እኩይ ዓላማውን ለመፈፀም በሚያደርጉት የጥፋት እንቅስቃሴ የክልሉ ሕዝብ ሠላም አንስተዋል።
በዚህም የቀድሞ የህወሓት ቡድን ጽምዶ የሚል የጥፋት ጥምረት በመፍጠር ኢትዮጵያን ለማዳከም ፍላጎት ካላቸው ኃይሎች ጋር እየሠራ መሆኑን አጋልጠዋል፡፡
በመሆኑም ይህ ቡድን በክልሉ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ማስቆም ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ቡድኑ በትግራይ ክልል ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል በማጋለጥ የህዝብ ድምፅ እንዲሆኑ ሚናቸውን እንዲወጡም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሠራዊት ሸሎ
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አታክልቲ ገ/ሥላሴ ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://youtube.com/watch?...

2 months ago