(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት (EEAS) ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፥ በሱዳን ኤል ኦቤይድ ከተማ ላይ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ። ሕብረቱ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) በከተማዋ ላይ የጀመሩትን መጠነ-ሰፊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ በጥብቅ አሳስቧል።
በመግለጫው ላይ ኤል ኦቤይድ ከተማ ቀደም ሲል ከፍተኛ ውድመትና ሰብአዊ ቀውስ ካስተናገደችው ኤል ፋሸር ከተማ ጋር ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊገጥማት እንደማይገባ ተመልክቷል። በአሁኑ ወቅት በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ፣ በብሔረሰቦች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት እና የሲቪል መሰረተ-ልማቶችን ኢላማ ያደረገው ውድመት በአስቸኳይ መቆም እንዳለበትም ሕብረቱ አስታውቋል።
አክሎም በከተማዋ የሚገኙ ንጹሃን ዜጎች ያለ ምንም ገደብ በነፃነትና በሰላም ቀጠናውን ለቀው መውጣት እንዲችሉ እንዲሁም ሰብአዊ ረድኤት አቅራቢ ድርጅቶች ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ያልተገደበ እርዳታ ማቅረብ የሚያስችላቸው ዕድል ሊመቻችላቸው እንደሚገባ የአውሮፓ ሕብረት በፅኑ አሳስቧል።

2 months ago