(ዘ-ሐበሻ ዜና) የታሂት ቾንግ የእግር ኳስ ህይወት ጉዞ "በጽናት መታገል እና ወደ ማንነት መመለስ" ለሚለው እጅግ አበረታች የሆነ ህያው ምስክር ነው። የህይወት መንገድ ሁልጊዜ ቀጥ ያለ መስመር አይደለም፤ ውጣ ውረዶች እና ያልተጠበቁ ምዕራፎች አሉት። የቾንግ ታሪክም የሚያስተምረን ይህንን ነው።
በኔዘርላንዱ ፌይኑርድ የጀመረው የልጅነት ህልሙ፣ ገና በ16 ዓመቱ ወደ ታላቁ ማንቸስተር ዩናይትድ አካዳሚ ሲቀላቀል እውን የሆነ ይመስል ነበር። በዚያም የክለቡን ታላላቅ የወጣት ተጫዋቾች ሽልማቶችን ጠቅልሎ በመውሰድ በብዙዎች ዘንድ ትልቅ ተስፋ ተጣለበት። እ.ኤ.አ በ2019 ደግሞ በኤፍ ኤ ካፕ የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል ጨዋታ በማድረግ ህልሙን አኖረ።
ነገር ግን በእግር ኳስ ዓለም ውስጥ ያለው እውነታ ሁልጊዜ እንደታሰበው አይሄድም። ታሂት የቋሚነት ቦታ ለማግኘት ባደረገው ትግል በውሰት ከሀገር ሀገር ተንከራትቷል፤ ወደ ጀርመኑ ቨርደር ብሬመን፣ ወደ ቤልጅየሙ ክለብ ብሩጅ፣ እንዲሁም ወደ እንግሊዙ በርሚንግሀም ሲቲ። ብዙዎች "ህልሙ እዚህ ላይ አከተመ" ብለው ሲያስቡ፣ እሱ ግን ተስፋ አልቆረጠም። በየሄደበት ቦታ ሁሉ ራሱን እያሻሻለ፣ ከውድቀት እየተማረ ጉዞውን ቀጠለ። በበርሚንግሀም ቋሚ ኮንትራት ፈርሞ፣ ቀጥሎም ወደ ሉተን ታውን አድጎ፣ አሁን ደግሞ በ2025 ሼፊልድ ዩናይትድን ተቀላቅሎ ጠንካራ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል። ከምቾት ቀጣና ወጥቶ መስራት እና አለመሰላቸት የት እንደሚያደርስ አሳይቷል።
ከሁሉም በላይ ግን የታሂት ቾንግ ታሪክ ልብ የሚነካው በብሔራዊ ቡድን ምርጫው ላይ ነው!
ታሂት ከ15 እስከ 21 ዓመት በታች ባሉ የኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ ከ40 ጊዜ በላይ ተሰልፎ ተጫውቷል። በታላቋ ኔዘርላንድስ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የመጫወት እድል እና ከፍ ያለ ስም የማግኘት በር ከፊቱ ተከፍቶ ነበር። እሱ ግን በ2025 የልቡን ጥሪ አዳመጠ። በዓለም ካርታ ላይ ጣት ለምታክል እና በዓለም ዋንጫ ታሪክ ከታዩ ሀገራት ሁሉ እጅግ ትንሿ ለሆነችው የትውልድ ሀረጉ ኩራሳዎ ለመጫወት ወሰነ!
ይህ ውሳኔ ትልቅ ትምህርት አለው። ስኬት ማለት ሁልጊዜ በታላላቅ መድረኮች ላይ መታየት ብቻ አይደለም፤ ስኬት ማለት ማንነትን አለመዘንጋት፣ ህዝብህ እና የዘር ሐረግህን በትንሹም ቢሆን ስትጠቅመው ማየት፣ እንዲሁም ለምትወደው ነገር በልበ ሙሉነት መቆም ጭምር ነው። ታሂት ቾንግ ትልቅ ስም እና ዝና ከሚያስገኝለት የኔዘርላንድስ ማሊያ ይልቅ፣ የኩራሳዎን ማሊያ ለብሶ ለሀገሩ ታሪክ መስራትን መረጠ።
የታሂት ቾንግ ጉዞ የሚነግረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ "ምንም ያህል ተሰጥኦ ቢኖረን፣ ፈተናዎች ሲገጥሙን በጽናት ማለፍ አለብን፤ ከየት እንደመጣን እና ማንነታችንን ደግሞ መቼም ቢሆን መርሳት የለብንም!"

2 months ago