የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያው የተዋሃደ አቀራረብን በመከተል በአፍሪካ ቀዳሚ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት ሥራ የጀመረው የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ የተዋሃደ አቀራረብን በመከተል በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ የሚያጣምረውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ በመሶብ አገልግሎት አማካኝነት ዜጎች በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ የሚያገኙበት የተቀናጀ ሥርዓት በመገንባት በአህጉሪቱ ተጠቃሽ የሆነ የቴክኖሎጂ ሽግግር እያስመዘገበች ነው።
በብዙ የአፍሪካ ሀገራት የዲጂታል አገልግሎት ሽግግር አሁንም በጥቂት ዘርፎች ወይም በተናጠል ተቋማት ብቻ የተወሰነ መሆኑን ገልጸው÷ እንደ መሶብ ያሉ በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ የተዋሃደ ሥርዓት በስፋት የሚያቀርብ ሞዴል በአህጉሪቱ ገና ያልተለመደ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ጉዞ ከአንድ ተነስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ 70 ቅርንጫፎች ማደጉ ልዩ ውጤት ነው፤ ይህ ስኬት በርካታ ሀገራት ካስመዘገቡት በላይ መሆኑንም አመልክተዋል።
የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ለማጠናከር አገልግሎቱን ከቋሚ ማዕከላት ወደ ተንቀሳቃሽ እና የሞባይል መድረኮች የማሸጋገር ሥራ መጀመሩን እና ይህም ዜጎች ለአገልግሎት ወደ ተለያዩ ማዕከላት ከመመላለስ ይልቅ ከየቤታቸው ሆነው በስልካቸው እንዲገለገሉ የሚያስችል ምቹ አቅጣጫ መሆኑን አስረድተዋል።
የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማቀላጠፍ ወደ አውቶቡስ መሶብ አገልግሎት መሸጋገሩን እና በዚህም ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በጋዝ እና ኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቅሳቀሱ አውቶቡሶችን በመሶብ ሥርዓት ውስጥ ማካተት መቻሉን አንስተዋል።
በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ የሚያጣምረው የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያም በሁሉም መስክ የተዋሃደ አቀራረብን በመከተል በአፍሪካ ቀዳሚው መሆኑን ነው ነው ያስረዱት፡፡
ይህ ሒደት የዲጂታል መንግሥት ግንባታን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በዮናስ ጌትነት

2 months ago