Logo
YenetaTube
በኮንጎ 75 የሕክምና ባለሙያዎች በኢቦላ ቫይረስ መጠቃታቸው ተገለፀ

የዓለም ጤና ድርጅት እንደገለጸው ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 75 የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሕክምና ባለሙያዎች በኢቦላ ቫይረስ ተይዘዋል።

አንድ ከፍተኛ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣን እንደገለፁት በቫይረሱ ከተጠቁ የህክምና ባለሙያዎች መካከል 17ቱ ህይወታቸው አልፏል ።

ብዙ የሕክምና ባለሙያዎች በሽታው
በይፋ ከመታወጁ በፊት ለበሽታው ተጋልጠዋል ተብሏል ።

አሁንም ቢሆን የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ለመከላከል የሚያስፈልጉ መሠረታዊ መሣሪያዎች አቅርቦት እጥረት እንዳለ ገልፀዋል ። ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.