(ዘ-ሐበሻ ዜና) አስመጪዎች በጉምሩክ ሲስተም በመላሸት የተነሳ ከፍተኛ ኪሳራና መጉላላት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ፡፡ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት ወይንም ኢኤስደብሊው ሲስተሙ ከተበላሸ አንድ ወር አስቆጥሯል፡፡ ኮሚሽኑ ግንቦት 20 ቀን 2018 በፃፈው ደብዳቤ በሲስተሙ ላይ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ችግሩ እስከሚፈታ ለአስመጪዎች በማንዋል አገልግሎት እንዲሰጥ የሚል መመሪያ አስተላልፏል፡፡ አስመጪዎች እንደሚናገሩት ይህ መመሪያ ንብረታቸውን በወቅቱ አውጥተው ለመስራት የሚያስችል ባለመሆኑ ለከፍተኛ እንግልትና ኪሳራ እየተዳረጉ ነው፡፡
አስመጪዎቹ ሲናገሩ ‹‹ይህ አሰራር ላኪዎችን ብቻ በመጥቀም አስመጪዎችን ሆነ ብሎ ለከፍተኛ መጉላላት አሳልፎ የሰጠ ይመስላል›› ያሉ ሲሆን ሲስተሙ ባለመስራቱ በጉምሩክ መስሪያ ቤቶችና በባንኮች ለረጅም ሰአታት ወረፋ በመጠበቅ ለድካምና እንግልት እንደዳረጋቸው አስረድተዋል፡፡ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገዟቸውና ወደአገር ውስጥ ያስገቧቸው እቃዎች በወቅቱ ባለመውጣታቸው በየወደቡና በየመጋዘኑ እየተበላሹና ለጉዳት እየተዳረጉ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ላኪዎች በማንዋል እንዲስተናገዱ እየተደረገ ባለበት ወቅት አስመጪዎችን በተመሳሳይ መንገድ ለምን ማስተናገድ አልተቻለም? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡
ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ይህ በጉምሩክና በባንኮች መካከል ያለው የአሰራር መጓተትና የአማራጭ መፍትሄ እጥረት በአስቸኳይ ካልተቀረፈ በአገሪቱ ውስጥ የገበያ አቅርቦትና የዋጋ ንረት ላይ የራሱን አሉታዊ ጥላ ሊያሳርፍ ይችላል፡፡

2 months ago