ኢቢሲ እና ቲቪ ብሪክስ የጋራ የሚዲያ ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በዓለም አቀፉ የብሪክስ የመረጃ መረብ ላይ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ለማሳደግ ከአለም አቀፉ የሚዲያ ተቋም ቲቪ ብሪክስ ጋር የአጋርነት ስምምነት አድርጓል።
ይህንን ስምምነት የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም ኤሮ እና የቲቪ ብሪክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጃና ቶልስቲኮቫ በጋራ በመሆን ፈርመውታል።
በተደረገው ስምምነት መሰረት ሁለቱ የሚዲያ ተቋማት የመረጃ፣ የዕውቀት እና የሰው ኃይል ልውውጥ የሚያደርጉ ሲሆን የብሪክስ አባል በሆኑ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጎሉ የሚዲያ ይዘቶችን በትብብር ያዘጋጃሉ።
በምክትል ሥራ አስፈጻሚ ማዕረግ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሞላልኝ መለሰ እንደገለጹት ይህ ስምምነት የኮርፖሬሽኑን የሚዲያ ባለሙያዎች የክህሎት እና የሙያ ብቃት ለማሳደግ ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
በሌላ በኩል የቲቪ ብሪክስ የአፍሪካ ቀጣና ኃላፊ ዩሊያ ናዛርኪና የኢቢሲ ጋዜጠኞች ያላቸው የዳበረ ልምድ የብሪክስን ዓለም አቀፍ የመረጃ ስርጭት ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።
ይህ የጋራ የሥራ ስምምነት ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን በቀጥታ እንድታገኝ የሚያስችላት ሲሆን ሀገራዊ ሁነቶችን፣ የአፍሪካን የበለጸገ ባህል እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮችን በዓለም አቀፍ የሚዲያ መድረኮች ላይ በስፋት ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
#ebc #tvbrics #brics #mediapartnership #media #news #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago