የመደመር አንቀጽ
አክራሪነት የሰማይን ዳርቻ ፍለጋ የሚደረግ ከንቱ ግሥጋሴ ነው። ሰማይን ስንመለከተው ከተራራው ወይም ከሩቅ ከሚታየው አንድ የተፈጥሮ ወይም ሰው ሠራሽ ነገር ጀርባ የተሸሸገ ጥግ ያለው ይመስለናል።
ነገር ግን ከአድማስ ጥጉ ለመድረስ እስከ ተራራው ጫፍ ብንጓዝም፤ ከሩቅ የሚታይ ሌላ የሰማዩ ዳር የሚመስል አዲስ አድማስ እናገኛለን። ከቀጣዩ አድማስ ጥግ ደርሰን ብንመለከትም ሰማይ ከምድር የተሰፋበት የሚመስል ሌላ ነገር ከሩቅ ይጠብቀናል፡፡
በዘመናዊቱ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ጉዞ ውስጥ፤ አክራሪነት ዓይነተኛ ኃይል ሆኖ ትውልዶችን የመፍጠርና የመቅረጽ ከፍተኛ ሚናው ቀጥሏል። አክራሪነት የአንድ ሐሳብ የመጨረሻ ጥግን መፈለግ ነው። አንዱ ዳር ሲደርሱ ሐሳብን እየለጠጡ ሌላ ጫፍ የመፈለግ።
የማያባራ የአንድ ጽንፍ ፍለጋ ጉዞ። ይህም አንድን ጥግ የመፈለግ ወይም ውል የሌለው ልዩነትን የመለጠጥ የማያባራ ጉዞ፤ በትብብርና በፉክክር መካከል ሚዛን የመሳት ውጤት ነው።
በአንድ በኩል ከእኔ ጋር ብቻ ተሰለፉ የሚል አላስፈላጊ ልሙጥ የሆነ ትብብር ፍለጋ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ እኔ ወይ አንተ ብቻ ትክክል ነን፤ የሚል የተወጠረ ፉክክርመልክ አለው፡፡ አክራሪነት “እኔን ምሰል” የሚል ጠቅላይነት እና “አትመስለኝም” የሚል አግላይነት ያቀፉት፤ ከራሱ የተጣላ የአስተሳሰብ ዝንባሌ ነው፡፡
የመደመር ትውልድ
ገጽ - 53

2 months ago