Logo
SeledaPost
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም በደቡብ አፍሪካ
የሚፈጸመውን የመጤ ጥላቻ ጥቃት ኮነኑ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም ገብረኢየሱስ በደቡብ አፍሪካ በቅርቡ ያገረሸውን የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ያተኮረ የጥላቻ ጥቃት አጥብቀው ኮንነዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ፤ በጥቃቱ ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን እና ሌሎች በርካቶችም ለደኅንነታቸው ሲሉ ለመሸሽ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ የተከሰተው ጥቃት «እጅግ ልብ ሰባሪ» መሆኑን ገልጸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ፓርላማ ያመሩበት ሰልፍ መደረጉን እና በሺዎች የሚቆጠሩ አባወራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን ጠቁመዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ፣ የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያውያን የተገደሉ ሲሆን፤ በተጨማሪም አምስት የሞዛምቢክ ዜጎች በሞሰል ቤይ አካባቢ ሕይወታቸው አልፏል።

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.