(ዘ-ሐበሻ ዜና) "በመጪው ምርጫ 33 ፐርሰንት ሩሲያዊያን ፑቲንን እንደማይመርጡ መረጃ አግኝቻለሁ" ሲሉ ዘለንስኪ ገለፁ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ የዛሬ መልእክታቸውን የጀመሩት ‹‹የዩክሬይንን ስለላ ስራዎች ለምትደግፉ ወዳጆቻችንና ጥብቅ መረጃ ለምትሰጡን ሁሉ አመሰግናለሁ›› በማለት ነው፡፡ ሲቀጥሉም የስለላ ተቋሞቻቸው በሩሲያ ያለውን ውስጣዊ ሁኔታ የሚመለከተ መረጃ እንዳደረሷቸው አስታውቀዋል፡፡
በመረጃው መሰረት ሩሲያዊያን በፕሬዝደንት ፑቲን እርምጃ ደስተኛ እንዳልሆኑ መረዳታቸውን ገልፀውም በመጪው ምርጫ 33 ፐርሰንት ያህሉ ሩሲያዊያን ፕሬዝደንቱን እንደማይመርጡ የሚያሳይ ዶክመንት እንዳለ አስታውቀዋል፡፡ ሾልኮ በወጣው መረጃ የፕሬዝደንቱን እርምጃ የሚደግፉት 55 ፐርሰንት መሆናቸውን ያስታወቁት ዘለንስኪ ‹‹ይህም የሩሲያ ገዢ ፓርቲ ተቀባይነት ከቀን ወደቀን እየወረደ መሆኑን የሚያሳይ ነው›› ብለዋል፡፡ የሩሲያ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርጫ የፊታችን ሴፕቴምበር 20 የሚከናወን ሲሆን ዘለንስኪ እንዳሉት በሚቀጥሉት ወራት ደግሞ 33 ፐርሰንቱ ሊጨምር ይችላል፡፡

19 hours ago