የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እድሳት ተጠናቆ ወደ ውድድር ሊመለስ መሆኑ ተገለጸ
የባሕር ዳር ዓለም ከባህር ዳር ከተማ ስታዲየም በቅርቡ ወደ ስፖርታዊ ውድድሮች እንደሚመለስ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው አስታወቁ።
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ይህንን የገለጹት በከተማዋ በደመቀ ሁኔታ በተካሄደው የ1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር መዝጊያ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
የስታዲየሙን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጎሹ እንዳላማው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የእድሳት ሥራ በአሁኑ ወቅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመው፣ ስታዲየሙ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን ማስተናገድ በሚችልበት ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
ከተማዋ ያሏትን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና አዳዲስ እየተገነቡ ያሉ መስተንግዶዎችን ያነሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ይህ መሰረተልማት ስታዲየሙንና ባህር ዳርን ሁሉ የተሟላላት ዘመናዊ የቱሪዝምና የስፖርት ከተማ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በከተማዋ የተካሄደውን የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ውድድሩ የባሕር ዳር ከተማ አስተማማኝ የሰላም ከተማ መሆኗን በተግባር ያረጋገጠበት መድረክ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ውድድሩ በባሕር ዳር እንዲካሄድ ውሳኔ ላስተላለፉና በቦታው ተገኝተው ለታደሙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮችም የከተማ አስተዳደሩን ምስጋና አቅርበዋል።
#አሐዱ

9 hours ago