Logo
Ethio telecom
🏃‍♀️🏃‍♂️ የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በቦቆጂ በድምቀት ተካሔደ!!

የ12ኪ.ሜ. ርቀት የሸፈነው ውድድር ከ100 በላይ አትሌቶችን፣ ከአዲስ አበባ ከ70 በላይ ተሳታፊዎችንና 2500 የከተማዋ ነዋሪዎችን አሳትፏል።

በተጨማሪም ተተኪዎችን ለማፍራት ያለመውና ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ታዳጊዎችን ያሳተፈው የ15ዓመት በታችና የ11ዓመት በታች ውድድሮች ሲካሔዱ የሕጻናት ውድድርም የዝግጅቱ ተጨማሪ ውበት ነበር።

የአገራችን አትሌቲክስ ለማሳደግና ተተኪዎች ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም ላለፉት 5 ተከታታይ ዓመታት በስያሜ አጋርነት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር እየሠራ የሚገኝ ሲሆን ወደ ፊትም በአትሌቲክሱ ዘርፍ የምናደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክረን እንቀጥላለን።
#ethiotelecomgreatbokojirun #greatethiopianrun #bokoji #telebirr #ethiotelecom

3 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.