የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ጋር በማበር አዲስ ጥቃት ለመሰንዘር አቅደዋል ተባለ
ኢትዮጵያ በትግራይ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ግንባር (ትህነግ) ውስጥ የሚገኙ አክራሪ አቋም ያላቸው አካላት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጁ ነው ስትል መክሰሰሷን ሶማሊ ሪፖርት ዘግቧል።
ይህ እቅድ አውዳሚውን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ የተገኘውን ደካማ ሰላም አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል መንግሥት አስጠንቅቋል። በአልጀዚራ በተሰማው መረጃ መሰረት፥ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የትህነግ መሪዎች ከጎረቤት ኤርትራ በሚያገኙት ድጋፍ በመታገዝ በሚቀጥሉት ቀናት ጥቃት ለመሰንዘር እያቀዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ክስ የቀረበው የ600 ሺህ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን የሁለት ዓመት ጦርነት ያቆመውን የ2022ቱን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በመጣስ ቡድኑ አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ እየሞከረ ባለበት ወቅት ነው ተብሏል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ትህነግን በፌዴራል መንግሥት የሚደገፈውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በማፍረስ፣ በምትኩ ሕገ-ወጥ የተባለ ክልላዊ አስተዳደር አቋቁሟል ስትል ከሳለች። ይህ ውንጀላ የመጣው ትህነግ ቀደም ሲል ታግዶ የነበረውን የክልል ምክር ቤት መልሶ ለማቋቋም ከወሰነ በኋላ ቢሆንም፥ ቡድኑ እስካሁን ለቀረበበት ክስ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም
በአዲስ አበባና በአስመራ መካከል ያለው ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተበላሸ መምጣቱ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚቀሰቀስ አዲስ አለመረጋጋት ለአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድ ሰፊ አንድምታ ሊኖረው ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሯል። ማንኛውም ዓይነት ወደ ከፍተኛ ውጊያ መመለስ አሁን ያለውን ተጋላጭ የሰላም ሂደት አደጋ ላይ እንደሚጥልና ቀጠናውን መልሶ ወደ አስከፊ ግጭት ውስጥ የመክተት ዕድል እንዳለው ተንታኞች ያስጠነቅቃሉ።

1 day ago