Logo
SeledaPost
በህወሓት ላይ እርምጃ ይወሰድ-ኢዜማ‼️
የፌዴራል መንግሥቱ ሕውሓት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ኢዜማ ጠየቀ‼️
አካሄዱ ‹መኢሶንን ይመስላል› በሚል የሚተቸው ኢዜማ በትግራይ ያንዣበበውን ወታደራዊ ውጥረት በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የፌዴራል መንግስቱ ሕውሓት ላይ እርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል፡፡ ሕውሓት ደርግን ጥሎ ስልጣን ከተቆጣጠረ አንስቶ የሰራቸውን ጥፋቶች የሚዘረዝረው መግለጫው፤ አሁን ላለው አገራዊ ችግር መንስኤው ሕውሓት ያሠፈነው የብሔር ፖለቲካ እንደሆነ አንስቷል፡፡

ለፕሪቶሪያ ስምምነት አለመተግበር እና ለተፈናቃዮች አለመመለስ ሕውሓትን ብቻ ተጠያቂ ያደገው የፓርቲው መግለጫ፤ ‹‹ይህንን ኃይል በቃህ ማለት እና በትግራይ ያሉ ወገኖቻችንን ከማያባራ መከራ መታደግ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን የጋራ የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል፤ ጦርነትን ሳይጀመር በፊት ማስቆም ይገባናል›› ሲል ጠይቋል፡፡

‹‹እንደ ሕወሓት ዓይነት ደም የማይጠረቃ አካል እና እሱን የሚዘውሩ ጥቂት ግለሰቦች በቃችሁ ብሎ ለማስቆም እና የትግራይ ህዝብን ካላስፈላጊ መከራ ለመታደግ በህዝብ ላይ ምንም አይነት መስዋዕትነት በማያስከትል መልኩ በሕገወጥ ቡድኑ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አስፈላጊ ሕጋዊ እርምጃ በመንግሥት እና ከመንግሥት ጋር በጋራ በሚቆሙ ማንኛውም ለትግራይ ማኅበረሰብ በሚቆረቆር አካል ሊወሰድ እንደሚገባ ያምናል›› በማለት ሕውሃት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.