የተፈጥሮ ድንቅ ውበት በልኩ የተገለጠበት ሥፍራ… ወንጪ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው ወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር እና ሎጅ የተፈጥሮ ድንቅ ውበት በሚገርም ሁኔታ የተገለጠበት ሥፍራ ነው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ነጋ ወዳጆ ፥ ወንጪ ተፈጥሮ፣ ታሪክ፣ ቅርስ እና ባህል በአንድ ተሰናስለው የሚገኙበት ድንቅ የቱሪስት መዳረሻ ነው ይላሉ፡፡
የአካባቢውን መልክዓ ምድር፣ የአኗኗር ዘዬ፣ ባህል እና ማንነት በማስተሳሰር ለሌሎች የቱሪስት መዳረሻዎች ምሳሌ በሚሆን መልኩ መገንባቱን አውስተዋል፡፡
ማራኪ ተፈጥሮ የሚስተዋልበትን ወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር እና ሎጅ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
በተለይም ለቱሪስቶች አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን ከማሟላት አንጻር በትብብር የተከናወነው ሥራ ውጤታማ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዚህ መሰረትም በቱሪስት መዳረሻው የትራንስፖርት፣ የማረፊያ ክፍሎች እና ሌሎች አገልግሎቶች መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል፡፡
በመንደሩ የልማት ተነሺዎች ለመቋቋሚያ የተሰሩላቸውን ደረጃቸውን የጠበቁ ቪላ ቤቶች ለጎብኚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እያከራዩ ገቢ ያገኛሉ ነው ያሉት፡፡
ይህም የቱሪስቶችን ቆይታ ከማራዘም ባለፈ ጎብኚዎች አካባቢውን በደንብ ተመልክተው አይረሴ ጊዜን እንዲያሳልፉ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አቶ ነጋ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የአካባቢውን ባህላዊ ምግቦች፣ ማር፣ የቡና አፈላል ሥርዓት እና ሌሎች ባህላዊ ክዋኔዎችን ለጎብኚዎች በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
አሁን ላይም በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች ወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን እየጎበኙ እንደሚገኙ ነው የገለጹት፡፡
የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን በመጎብኘት አይረሴ ጊዜ እንዲያሳልፉም ጥሪ አቅርበዋል።

3 days ago